‘’ የፕሬስ ነጻነት ቀን ስናከበር ጋዜጠኞች ለአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል‘’ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ መገ…

‘’ የፕሬስ ነጻነት ቀን ስናከበር ጋዜጠኞች ለአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ተግባራዊ ምላሽ በመስጠት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል‘’ ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ምክር ቤት የ2016 የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት መግለጫ አውጥቷል፡፡

ምክር ቤቱም ለጣያብችን ኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ የዘንድሮው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ‘’ጋዜጠኝነት በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ” ወይም “Journalism in the face of the Environmental Crisis” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገፃል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ አማካይነት በየዓመቱ ሚያዝያ 25 ወይም ሜይ 3 የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም ዙሪያ ያለውን የፕሬስ ነፃነት ሁኔታ ለመገምገም፣ መገናኛ ብዙሃን በነጻነታቸው ላይ ከሚሰነዘረው ጥቃት ለመከላከል እና ህይወታቸውን ላጡ ጋዜጠኞች ክብር ለመስጠት የሚከበር በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃንና የፕሬስ ነፃነት አቀንቃኞች ዕለቱን በተለየ ሁኔታ ይመለከቱታል ተብሏል፡፡

የአየር ንብረት እና የብዝሃ ህይወት ቀውስ በአካባቢ እና ስነ–ምህዳር ላይ ብቻ ሳይሆን በአለም ዙሪያ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየጎዳ ነው፤ በዚህም በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ውስጥ ሃገራችን የጉዳቱ ገፈት ቀማሽ ከመሆንዋም ሌላ ችግሩን ለመቅረፍ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ትገኛለች የሚለው መግለጫው፡፡

በዚህ ረገድ ባለፉት በርካታ አመታት በሃገራችን ቀላል የማይባሉ ጥረቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን በተለይ ባለፉት 5 አመታት የተከናወኑ የአካባቢ ጥበቃ ጥረቶች ቀላል አይደሉም፡፡

በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች የሚተከሉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርና በየአካባቢው የሚካሄደው የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ በሀገራችን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት መካከል ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በዚህ ውስጥ የሃገራችን መገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ቀላል የማይባል ሚና ተጫውተዋል፡፡

የሀገራችን መገናኛ ብዙሃን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ የመጡ አካባቢያዊ ለውጦችን በማጠናከር፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ህጐች፣ አሰራሮችና ለአካባቢ ደህንነት ጠንቅ የሆኑ አመለካከቶች ላይ በመወያየት ትኩረት እንዲያገኙ ሲጥሩ ጋዜጠኞች ሥራቸውን ከስጋትና ፍርሃት ነፃ ሆነው በኃላፊነት ስሜት የሚሰሩበት ሁኔታ ትኩረት ሊስጠው እንደሚገባ ምክር ቤታችን ያምናል ሲል በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply