You are currently viewing የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ቢደረግስ ምንድነው ችግሩ? ~~~~~~~~ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ~~~~~~~~~~ ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 18/2014 ዓ.ም…                    አሻራ ሚዲ…

የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ቢደረግስ ምንድነው ችግሩ? ~~~~~~~~ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ~~~~~~~~~~ ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 18/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲ…

የፖለቲካ ነጥብ ለማስቆጠር ቢደረግስ ምንድነው ችግሩ? ~~~~~~~~ ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ~~~~~~~~~~ ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 18/2014 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የተከበሩ ዶ/ር ደሳለ ጫኔ ያቀረቡትን አስቸኳይ አጀንዳ ላለመቀበል ስለፈለጉ ብቻ ሳይፈቀድ መናገር አይቻልምና ማይኩን ይዘጉት በማለት ማስፈራራት በሚመስል የቁጣ አጋገራቸው ዕድል በመንፈጋቸው ምክንያት የተከበሩ ዶ/ር ደሳለ ጫኔና ጓዶቻቸው ስብሰባውን ትተው መውጣታቸው ይታወቃል። ይህም ተገቢ ምላሽ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው። ይልቁንስ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት አቶ ክርስቲያን ታደለ አብረው ሳይወጡ መቅረታቸው ነው እኔን የገረመኝ፣ ሪፖርት ለማቅረብ ምናምን ብሎ ነገር በምክንያትነት ሊቀርብ አይገባውም። ይህን ሁኔታ ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥቷል፣ የመግለጫው መሪ ቃልም “የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውይይትና የምክክር እንጂ የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ መድረክ መሆን የለበትም” የሚል ነው፡፡ ከሞቱ አሟሟቱ እንደሚባለው የቀደመው አሳፋሪ ስህተት አልበቃ ብሎ ይህን መግለጫ መስጠቱ በራሱ ይበልጥ ያሳዝናል። በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአሰራር ስነ ስርአት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 33 መሰረት በእለታዊ አንጀንዳ ያልተቀረጸ ነገር ግን የአፈ ጉባኤውን ፈቃድ ያገኘ ለህዝብ ጠቀሜታ ያለው አስቸኳይ ጉዳይ በአባላት ወይም በፓርላማ ቡድን ቀርቦ ውይይት ሊደረግበት እንደሚችል ይታመናል፡፡ ይህን ደንብ መነሻ ካደረግን የተከበሩ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ያቀረቡት እለታዊ አጀንዳ የህግም ሆነ የአሰራር ስህተት የለበትም ማለት ነው፡፡ እውነታው ይኸ ከሆነ አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ለምን ይሆን ዶ/ር ደሳለኝን ተገቢ ባልሆነ መልኩ የከለከሏቸው? አጀንዳው ያን ያህል የህዝብ ጥቅም አያስገኝም በማለት አሳንሰው አይተውት ይሆን? ይህም ሆኖ አንድ ሰው የፖለቲካ ዓላማ ለማስፈጸም በሕዝብ ተመርጦ ወደ ም/ቤት ሲገባ እያንዳንዱን አጋጣሚ በመጠቀም ለወከለው ሕዝብ ድምጽ ለመሆን ነው። በዚህም የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሩ አይቀርም፣ እናም ይኸ ሁኔታ እንደነውር ተቆጥሮ የስህተት ማረሚያ መግለጫ መሪ ቃል ሆኖ መምጣት ነበረበትን? ከአንድ ልምድ ካለው ም/ቤት ከፍተኛ አመራሮች ይሄ ድርጊት የሚጠበቅ አይደለም። በዚህም የም/ቤቱ አመራሮች ሁለተኛ ስህተት በመፈጸም ይበልጥ ትዝብት ውስጥ ከመግባታቸውም በላይ ሕዝብ በግፍ እየተጨፈጨፈ ባለበት ሁኔታ እነሱ ለሥነ ሥርአት ህግ መከበር አለመከበር ያን ያህል መጨነቃቸው በእጅጉ ያሳፍራል። ያውም የሥነ ሥርአት ችግር በሌለበት አቀራረብና የቀረበው አጀንዳም እጅግ ወቅታዊና አሳሳቢ ሆኖ እያለ። እንዳው ይሁንም የዶ/ር ደሳለኝ አቀራረብ ስህተት ነበረበት ከተባለም በተረጋጋና የሥነ ሥርአት ደንቡን በሚያስገነዝብ መልኩ ንግግራቸውን ለማስቆም ጥረት ማድረግ እየተገባ በቁጣና ፊትን በማኮሳተር አንድን የተከበሩ የም/ቤት አባል ማይኩን ይዝጉት እያሉ ማሳጣት ተገቢ ነውን? ይባስ ብለው ይሉሽን ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ እንደሚባለው ስህተቱን እነሱው ፈጽመው እያለ ሌላውን ለማሳጣት መሞከር ራስን እንደማታለል ይቆጠራልና ትምህርት ሊወሰድበት ይገባል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply