የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስንደግፍም ሆነ ስንቃወም ልንከተላቸዉ የሚገቡ ምርሆዎች =========== ሸንቁጥ አየለ ———– 1. ልንደግፋቸዉ እና ልንተባበራቸዉ የሚገቡ ሀይሎች የሚከተሉት…

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስንደግፍም ሆነ ስንቃወም ልንከተላቸዉ የሚገቡ ምርሆዎች =========== ሸንቁጥ አየለ ———– 1. ልንደግፋቸዉ እና ልንተባበራቸዉ የሚገቡ ሀይሎች የሚከተሉትን መርሆዎች የሚከተሉ ናቸዉ… ———————– 1.የኢትዮጵያ ህዝብ በነገድ ቢለያይም አንድ ህዝብ ነዉ ብለዉ የሚያስተምሩ 2.ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ሳይሆን የተፈጠረችዉ በኢትዮጵያዉያን መሃከል በተፈጠረ መስተጋብራዊ የታሪክ ሂደት ነዉ ብለዉ የሚያስተምሩ 3.የትኛዉንም ነገድ በቅኝ ገዥነት/በዝባዥነት/መጤነት የማይከሱ 4.የወያኔን ህገመንግስት/ክልል ለማፍረስ የቆረጡ 5.በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ 6.የፖለቲካ አስተምህሮቱ ኢትዮጵያዉያንን ለተጨማሪ እልቂት የማይዳርግ 6.1 ህዝቡን በሀይማኖት የማይከፋፍል 6.2 አንዱን መጤ አንዱን ነዋሪ ነገድ በማድረግ እርስ በርሱ ህዝቡን ለጭፍጨፋ የማያዘጋጅ 7.ኢትዮጵያዊ ነገዶችን ሁሉ እኩል የሚወድ እና የሚያከብር 8.በነገዳቸዉ ተደራጅተዉ የጎሳ ፖለቲካ ቢያራምዱ እንኳን ሌሎች ነገዶችን ለማጥፋት ያለመ እንቅስቃሴ የማያደርጉ II. የሚከተሉትን መርሆዎች ከሚከተሉ ሀይሎች ጋር መተባበርን እና ፖለቲካ መስራት የሚፈልግ አማራ በጠላት ወጥመድ ዉስጥ የገባ ነዉ:: የሚከተሉትን መርሆዎች የሚከተል ቁልፍ ጠላት እንጂ ወዳጅ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም =================== 1.አማራ በዝባዥ መደብ ነበር ብለዉ 2.አንዱ ነገድ ለአንድ አካባቢ መጤ ሌላዉ ነገድ ደግሞ ለአንድ አካባቢ ነዋሪ ነዉ ብሎ የሚያስብ 3.የኢትዮጵያን አንድነት በቅድመ ሁኔታ ላይ ያስቀመጠ ወይም የኢትዮጵያን አንድነት የሚክድ 4.ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት/በወረራ ተፈጥራለች ብለዉ የሚሉ 5.አማራ ሲታረድ/ሲፈናቀል አማራ ብላችሁ ከዘገባችሁ ሀገር ይፈርሳል ሲሉ ከቆዩ ብኋላ አማራ መደራጀት ሲጀምር አማራ የሚባል ነገድ የሚባል የለም የሚሉ 6.አንዱን(የትኛዉንም ቢሆን) ኢትዮጵያዊ ነገድ የሚጠላ::የኢትዮጵያ ህዝብ የተለያዬ ህዝብ ነዉ ብለዉ የሚያስተምሩ 7.የወያኔን ህገመንግስት/ክልል እና የወያኔ ጭፍሮችን(ኢህ አዴግ/ኦነግ/ብአዴን/ኦህዴድ) እንዲሁም አጋር ድርጅቶች የሚያራምዱትን የፖለቲካ ፍልስፍና የሚቀበል ሀይል 8.በኢትዮጵያ አንድነት ተደራጅቻለሁ ብለዉ ሲያበቁ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 ካሉት ዉስጥ አንዱን መርሆ የሚቀበሉ እነዚህን መርሆዎች ከሚከተሉ ሀይሎች ዛሬ ወዳጅ መስለዉ አብረዉህ ቢቆሙም የመጨረሻ ግባቸዉ አንተን ማጥፋት ነዉ::ስለዚህ ወዳጅነት ከጊዜአዊ ጥቅም ይልቅ በመርህ ላይ መመስረት አለበት::

Source: Link to the Post

Leave a Reply