የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ በነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነአድ) በኩል ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ፓርቲው አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ በነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነአድ) በኩል ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ፓርቲው አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ በነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነአድ) በኩል ፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ፓርቲው አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነአድ) ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ለአማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ በላከው መግለጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ እንዳሳዘነውና ግርምትም እንደፈጠረበት አስታውቋል። መግለጫው ፍፁም ተቀባይነት የለውም ያለው የነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነአድ) ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ የማዕከሉን ህግ እና አሰራር አልቀበልም ብሎ በራሱ ጊዜ ምርጫ አካሂጃለሁ ያለን የህወሀት ቡድንን በተመለከተ የሰጠውን መግለጫ አውግዞታል። ነአድ በህወሀት ቡድን ግንባር ቀደም አስተባባሪነት አማራ የአገር ጠላት እንደሆነ ተደርጎ ባላቋረጠ ሁኔታ ጭፍጨፋ ሲካሄድበት አንድም ድምጽ ያላሰማ ምክር ቤት መሆኑን በመጥቀስም ወቅሷል። በአገር መከላከያ ኃይል ላይ ግልጽ ጦርነት የከፈተን የወንበዴ ቡድንን አንድ እራሱን የቻለ መንግስት ወይም ኃይል እንደሆነ በማድረግ ከሉአላዊ አገር መንግስት ጋር እኩል “ሁሉቱም ወገኖች” ሲል የሰጠው መግለጫ ቃታ ስበው ከሚገድሉን ወንበዴዎች ያልተናነሰ በሞታችን ላይ ነዳጅ፣ በቁስላችን ላይ ጨው የመነስነስ ያህል ተስምቶናል ብሏል የነአድ ስራ አስፈጻሚ በላከው መግለጫ፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ እንዲሰራ ተቀርጾ የተሰጠውን ስራ አድምቶ በመስራት ፋንታ በተደጋጋሚ ቀይ መስመር የዘለለ ያልተገባ ስራዎች ሲሰራ የቆየና ያልተገባ አሰራሩን እንዲያርም ደጋግመው ጠይቀውት ለማስካከል አለመቻሉን ነአድ አውስቷል። ከልምድ እና ከአቅም ማነስ የተፈጠረ ይሆናል በሚል ክፍተቶቹን በቅንነት የማየት ሁኔታዎችም እንደነበሩ የጠቀሰው ነአድ እየዋለ እያደር ስናየው ግን ከዚህ ፍፁም የተለየ ሆኖ አግኝተነዋል ብሏል። በወለጋ ጉሊሶ እና ይህን የህወሀት የእብሪት ጦርነትን አስመልክቶ በሰጠነው የአቋም መግለጫ ጥቃቱ የግል ወይም ቡድን ላይ የተፈፀመ ሳይሆን አገርን ለማፍረስ የመጨረሻው መጀመሪያ ሆኖ ከማንኛውም ወረራ የከፋ ሲል መንግስት ከሰጠው መግለጫ ጋር የተመሳሰለ አቋም መያዛችን ይታወቃል ብሏል፡፡ ነአድ እንደ ፖለቲካ ድርጅት በጋራ ተሳትፎ ያቋቋመው የጋራ ምክር ቤት ቢሆንም እራሱን አግዝፎ ማየቱ እና እየሰሩ ያሉት ያልተገቡ ስራዎች በወቅቱ ባለመታረማቸው እንደ ወንበዴው ወያኔ ምክር ቤቱም ይኸው መንግስትን እና ወንበዴን ሟችና ገዳይን ያለዬ መግለጫ መስጠት ላይ ደርሷል ነው ነአድ በመግለጫው። ም/ቤቱ የሰጠውና የያዘው አቋምና መግለጫም ከድብቅ አላማ የመነጨ ነው ብለን እናስባለን ያለው ነፀብራቀ አማራ ድርጅት (ነአድ) በፊትም በተለያዩ ሚዲያዎችና ታላላቅ ስብሰባዎች ደግመን እንደገለፅነው ኢትዮጵያን በማዳን እና በማጥፋቱ ረገድ ጎራ የለየ ቁስል ያፈረጠ ትግል እንዲደረግ ማሳሰባችንን ለማስታወስ እንወዳለን ብሏል። ኢትዮጵያ ላሳለፈቻቸው ዘግናኝ ችግሮችም ሆነ ለአሁኑ ጦርነት ትህነግ ዋናው ተጠያቂ ነው ያለው ነአድ በወያኔ የተከፈተው ጦርነትን የእርስ በርስ ነው ብሎ የሚያስብ ቢኖር የተሳሳተ ሀሳብ የሚያራምድ ነው ብሏል። በመሆኑም ነአድ ጦርነቱ በድል እስኪጠናቀቅ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆሙን ነው ዳግም ያረጋገጠው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply