የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ የህግ አስፈጻሚ አካላት ላይ ክስ ይመስረት—ምርጫ ቦርድየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤን ያሰናከሉ የህግ አስፈ…

የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ የህግ አስፈጻሚ አካላት ላይ ክስ ይመስረት—ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤን ያሰናከሉ የህግ አስፈጻሚ አካላት ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር ክስ እንዲመሰርት ጠይቋል።

በመንግስት መስሪያ ቤቶች ስር የሚተዳደሩ ስብሰባ ቦታዎች እና አዳራሾች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ክፍት እንዲሆኑም ውሳኔ አሳልፏል።

ቦርዱ ይህን ያስታወቀው፤ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ያጋጠሙ መስተጓጎሎችን በተመለከተ ዛሬ ረቡዕ መጋቢት 5፤ 2015 በአዲስ አበባው ሃይሌ ግራንድ ሆቴል በሰጠው መግለጫ ነው።

በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ መሰረት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ቢያንስ በሶስት ዓመት አንድ ጊዜ ማካሄድ አለባቸው።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህን ግዴታቸውን ለመፈጸም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወቅት መስተጓጎል እየገጠማቸው እንደሚገኝ ምርጫ ቦርድ መግለጹን የኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘገባ ያመለክታል፡፡

ባለፈው እሁድ ጠቅላላ ጉባኤውን ሊያካሄድ የነበረው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ፤ ስብሰባውን ሊደርግበት የነበረበት ጋምቤላ ሆቴል ስብሰባውን ማስተናገድ እንደማይችል በመግለጹ ጉባኤውን ሳያካሄድ ቀርቷል።

እናት ፓርቲም በተመሳሳይ መልኩ ከሳምንት በፊት የካቲት 26 ሊያካሄደው የነበረው ጠቅላላ ጉባኤ መስተጓጎሉ ይታወሳል። የፓርቲው ፕሬዝዳንት በዕለቱ በሰጡት መግለጫ “ ‘ከበላይ አካል በመጣ ትዕዛዝ መሰብሰብ አትችሉም’ መባላቸውን ማሳወቃቸው ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መጋቢት 06 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply