የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ ዝግጅትን እየጎበኙ ነው

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ ዝግጅትን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተደረገውን የቁሳቁስ ዝግጅት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፤ በማሳያነት የተዘጋጁ የምርጫ ጣቢያዎችና ቁሶችን ነው እየጎበኙ የሚገኙት።

በጉብኝቱ ላይ በምርጫ ቦርድ በኩል ቀደም ብለው በተካሄዱ ምርጫዎች ጥቅም ላይ የዋሉ ቁሶችን ለዘንድሮ ከተዘጋጁት ጋር በማነጻጸር ገለጻ ተደርጓል።

በዚህም ለስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ የተዘጋጁ የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎችና ሌሎች ቁሶች ዘመናዊ ከመሆን ባለፈ ለግልጽነት የሚያግዙ ናቸው ተብሏል።

በዛሬው የጉብኝት መርሃ ግብር ምርጫ ቦርዱ ፓርቲዎች የተለያዩ ሥራዎችን የሚያከናውኑበትን የማዕከል ቢሮ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤትና የሴት ፓርቲ አባላት እንደሚያስረክብ ኢዜአ ዘግቧል።

The post የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቁሳቁስ ዝግጅትን እየጎበኙ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply