የ ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በዋሻ_ውስጥሲኖሩ ለነበሩ ሰወችየቤት መስሪያ ቆርቆሮ ድጋፍ አደረገ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 10/2014ዓ.ም አሻራ…

የ ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በዋሻ_ውስጥሲኖሩ ለነበሩ ሰወችየቤት መስሪያ ቆርቆሮ ድጋፍ አደረገ። ባህርዳር ። ሚያዚያ 10/2014ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በዛሬው ቀን ሰሜን ወሎ ዋድላ ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ቤታቸው ለፈረሰባቸው 28 አባውራወች 600,000 ብር /ስድስት መቶ ሺ ብር / ወጭ የተደረገበት ለ1 አባውራ 42 የቤት ቆርቆሮ በድምሩ -1176 የቤት መስሪያ ቆርቆሮ የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ድጋፍ አድርጓል። ይሄ ስራ እንዲሳካ በገንዘብ የደገፉ -በካናዳ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ (ECNAS) እና -በአሜሪካ ዋሽንግተን እስቴት ሲያትል ግብረሀል ሲሆኑ ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖች ስም ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት ከልብ ያመሰግናል ብሏል ። የዋድላ ወረዳ በትግራይ ወራሪ ሀይል ለ5 ወር የተያዘ እና ለ5 ግዜ ከፍተኛ ጦርነት የተደረገበት ቦታ በመሆኑ የብዙ ንፁሃን ሂወት የጠፋበት እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ ውድመት የደረሰበት ሲሆን በወረዳው የወደሙ ቤቶች አጠቃላይ ቁጥር 2776 ቤቶች ሲሆኑ በአንድ ቀበሌ ብቻ በ017 ከወደሙ 360 ቤቶች መካአል 180 ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ሰወቹ መጠለያ በማጣት እስከ አሁን ድረስ በዋሻ ውስጥ ለመኖር ተገደዋል። በሀገር እና በውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን መጭው የክረምት የዝናብ የብርድ ግዜ ከመምጣቱ በፊት እነዚህን ወገኖች መጠለያ እንዲያገኙ መንግስት እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥረት እንዲያደርግ ድርጂቱ ጥሪ አቅርቧል ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply