የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጭው ሳምንት ይጀመራል

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጭው ሳምንት ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጭው ሳምንት እንደሚጀመር የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ምዝገባው ከጥቅምት 16 እስከ 30 ቀን 2013 ዓ.ም በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚካሄድ ነው የትምህርት ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡
የፈተና ምዝገባ ሂደቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማካሄድም በተዘጋጀው ሶፍትዌር ላይ ምዝገባ ለሚያከናውኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጅ ባለሙያዎችና የፈተና ክፍል አስተባባሪዎች በየክልል ከተሞች ስልጠና መሰጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የ2012 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በቀጥታ የኢንተርኔት ኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

The post የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ በመጭው ሳምንት ይጀመራል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply