የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጄንሲ ገለጸ፡፡

ከትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የ12ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን ኤጀንሲው ገልጧል፡፡ፈተናው በበይነ መረብ (በኦን ላየን) እንደሚሰጥ የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

ለፈተናው የሚያስፈልጉ የግብዓትና የስልጠና ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር በተገናኘ ለሁሉም ተማሪዎች ስልጠና እንደሚሰጥ የተናገሩት ዶክተር ዲላሞ ቀደም ብለው የተሰጡ ፈተናዎች ለተማሪዎች መለማመጃነት እንደሚውሉም ጠቁመዋል፡፡

***********************************************************************

ቀን 19/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጄንሲ ገለጸ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply