የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።ትላንትና ሀሙስ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በ ” አምቦ መስክ ” ቀበሌ አቅጣጫውን ከባ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/DnJSvRfpCGecHPWudhWenHINn3wbq0YBTgFJFaA_oGDS8y3pRd4EID_7hYhMt49i9Idwsu1VByW-T2NUZDMLTKcryT6YnDQGE61KUNu8g31mlsyjiInDBJBcuh0fttukh3-oyy8Q41YdzNqgYpaoPJmmbYkmVuSPv7LEQEwYF5EecTM7NwPubyT14hJJaLUlhJ6WPcdZnK5VhrfV7JYEX9nUFC38LIYJQrIMrbJHGGDZlcxERelLi_RABJzJ1SzFCS1qwC5rquKipeXA_6UjiR8KHKo7RIbz04K_MyCOJSdv4gQBs3DgGMQH6dOKDM4GcncK_N1MPb_D_LNwPL0RXg.jpg

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶ በተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ትላንትና ሀሙስ በሰሜን ሜጫ ወረዳ በ ” አምቦ መስክ ” ቀበሌ አቅጣጫውን ከባህር ዳር ወደ ማርቆስ ያደረገ ሰሌዳ ቁጥር ” አማ 17492 ” የሆነ ተሽከርካሪ ወይም ኮስትር ተሽከርካሪ እና መነሻውን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ያደረገ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በተሳፋሪዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው በአምስት ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ከፈተናው የሚያግዳቸው አይደለም ተብሏል።

የሰሜን ሜጫ ወረዳ ትራንስፖርት ፅ/ቤት ግጭቱ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት መፈጠሩን ገልጿል።

በዚህ ወቅት ከአገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር ተያይዞ የትራፊክ መጨናነቅ ስላለ አሽከርካሪዎች በተገቢው ፍጥነት በማሽከርከር እራሳቸውን እና ተሳፋሪውን ከትራፊክ አደጋ እንዲታደጉ የሰሜን ሜጫ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አሳስቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply