የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሠራዊት አባላት የመፈተኛ ጊዜ ተራዘመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ…

የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሠራዊት አባላት የመፈተኛ ጊዜ ተራዘመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በመከላከያ ህብረት ስልጠና ዋና መምሪያ የአጠቃላይ ትምህርት መምሪያ እንዳስታወቀው ፣ በ2012 የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተናን ከየካቲት 29 ቀን 2013 ጀምሮ መውሠድ የሚገባቸው የሠራዊት አባላት በህግ ማስከበር ተልዕኮ ምክንያት ፈተናውን መውሰድ ስለማይችሉ ጊዜው መራዘሙን አስታውቋል ። የመምሪያው ሃላፊ ተወካይ አቶ ጌታሁን ሳህለየሱስ እንደገለፁት ፣ ጥቅምት 24 ቀን በሠራዊታችን የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ዘመቻ ምክንያት ፣ ሠራዊቱ በኦንላይን መመዝገብና አሁን ላይም መፈተን የማይችል መሆኑን በመገንዘብ ሊራዘም ችሏል። የመከላከያ ሚኒስቴር ለትምህርት ሚኒስቴር ችግሩን ቀድሞ በደብዳቤ በማሳወቅ እና ተገቢ መልስ በማግኘቱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሠራዊት አባላት ከሶስት ወር በኋላ ፈተናውን እንደሚወስዱ አቶ ጌታሁን ተናግረዋል። ይህን መነሻ በማድረግም መልዕክቱ ለክፍሎች በደብዳቤ የደረሰ ሲሆን ፣ ፈተናው በሚሠጥበት ወቅትም ቅድሚያ የማሣወቅ ስራ እንደሚሠራ አቶ ጌታሁን ሳህለየሱስ አስታውቀዋል ሲል መከላከያ በይፋዊ የትስስር ገጹ አጋርቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply