የ157 ሰዎች ህይወት ያለፈበት የ737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ምክንያት ኢማክስ የተባለ መቆጣጠሪያ መሆኑ ተገለፀ።በ2011 ዓ.ም. በቢሾፍቱ አቅራቢያ ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ያለፈ…

የ157 ሰዎች ህይወት ያለፈበት የ737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ምክንያት ኢማክስ የተባለ መቆጣጠሪያ መሆኑ ተገለፀ።

በ2011 ዓ.ም. በቢሾፍቱ አቅራቢያ ተከስክሶ የ157 ሰዎች ህይወት ያለፈበት የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ መንስኤ ኢማክስ (EMACS) የተባለው መቆጣጠሪያ ችግር መሆኑ ተገልጿል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በስሩ ከሚገኘው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ የአደጋውን የመጨረሻ ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።

ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደገለፁት የበረራ ሙያተኞቹ እና አውሮፕላኑ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ለበረራ ዝግጁ መሆናቸው የተረጋገጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም የጭነት ክብደቱም ለአደጋ የሚያጋልጥ እንዳልነበረ ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል።
አደጋው የተከሰተው በአውሮፕላኑ ውስጥ የሚገኝ ኢማክስ (EMACS) የተባለ መቆጣጠሪያ ችግር እንደሆነ ተረጋግጧል።

መሳሪያው የኤርፖርት እና የኤሌክትሮማግኔቲክ አካባቢ ትንተና እንዲሁም የአየር ማረፊያ እና የኤሌክትሮማግኔቲክ ጣቢያ ማረጋገጫን ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑን ማወቅ ተችሏል።

በዓለም አቀፍ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ደንብ መሰረት አደጋ በደረሰ በ12 ወራት ውስጥ ያለበት ደረጃ ሪፖርት ካልቀረበ አደጋውን ለመመርመር ኃላፊነት ያለበት ሀገር የምርመራ ውጤቱን እንዲያሳውቅ ይደነግጋል።

በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ እንዳስታወቀው የምርመራ ስራው በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝና ሌሎች አስገዳጅ ምክንያቶች ሊዘገይ መቻሉን ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply