የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም…

የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን ሦስት የትምህርት ሴሚስቴር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ገልጿል። ተማራቂ ተማሪዎች በቀሪዎቹ አጭር ወራት ውስጥ ያልተጠናቀቁ የትምህርት እና ሥልጠና ተግባራትን በተቻለ ቅልጥፍና እና ዝግጁነት በማጠናቀቅ ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም እንዲትቀላቀሉ እና የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ አሳስቧል። ሌሎች በ2013 ትምህርት እና ሥልጠና ዘመን ሙሉ ዓመቱን በተቋማት ቆይታ የሚደርጉት ተማሪዎች በሙሉ፣ ትምህርታቸውን በአግባቡ እየተማሩ ለአገራችን እና ለሕዝባችን አንድነት እና ኅብረት እንዲሁም ብልጽግና ጉዞ ፋይዳ ያላቸው ሰብአዊ እና ማኅበራዊ በጎ አድራጎት ተግባራት እና አገልግሎቶች በንቃት በመሳተፍ ወገንተኝነታቸውን እንዲገልጹ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጥሪ አድርጓል። የከፍተኛ ትምህርት እና ሥልጠና ማኅበረሰብ በሙሉ የተለመደውን ቀና ድጋፍ እና ትብብር በማከል የ2013 ትምህርት እና ሥልጠና ዘመን የተሳካ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ከአደራ ጭምር አሳስቧል ሲል ዋልታ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply