የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ተጀመረ

የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ በኦንላይን ተጀምሯል።

የኦንላይን ምዝገባውም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀረጓ ማሞ ተናግረዋል።

ተማሪዎችም በየአካባቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች በመገኘት በወቅቱ ምዝገባቸውን እንዲያከናውኑ ዳይሬክተሯ አሳስበዋል።

በዛሬው ዕለት የጀመረው ምዝገባውም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥል ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በከሮና ቫይረስ ምክንያት ሳይሰጥ የቀረው የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ዘንድሮ በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

The post የ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈታኞች ምዝገባ ተጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply