የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ

የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 20ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያለምንም የፀጥታ ችግር መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ለውድድሩ በሰላም መጠናቀቅ የከተማው ነዋሪዎች፣የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፣የፌዴራል ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ፣ የፕሮግራሙ አዘጋጆችና የተሳታፊዎች አስተዋፅዖ የላቀ እንደነበር ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለዚህም ኮሚሽኑ ለሁሉም አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡
10 ኪሎ ሜትር በሸፈነው እና መነሻውን መስቀል አደባባይ መድርሻውን ደግሞ አክሱም ህንፃ አካባቢ ያደረገው ሩጫው የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡
በዚህም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለሁሉም አካላት ምስጋና አቅርቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply