የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት 786 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

ሐሙስ ሰኔ 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባው 786 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ያካሄደ ሲሆን፥ የምክር ቤቱ አባላት በበጀቱ ላይ ያላቸውን ጥያቄዎች ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ለቀረቡትም ጥያቄዎች የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የፕላን ፋይናንስና በጀት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል።

በመቀጠል ምክር ቤቱ በፕላን ፋይናንስና በጀት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አማካኝነት በበጀቱ ዙሪያ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር፤ በአራት ድምጸ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ የውሳኔ ቁጥር 1275 /2014 አድርጎ አጽድቆታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም፥ የ2015 የፌደራል መንግስት በጀት፥ ብድር መቀነስ፣ የበጀት ጉድለት መቀነስ፣ ያለን ሀብት በቁጠባ መጠቀም እና የዋጋ ንረትን ማረጋጋት የሚሉ ነጥቦችን የትኩረት አቅጣጫውን ማድረጉን ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply