ኢትዮጲያ በዓለም ደስታ ከራቃቸዉ ሀገራት ዝርዝር ዉስጥ በ14ኛ ደረጃ ተቀመጠች፡፡
ለስድስት ተከታታይ ዓመታት ፊንላንድ በአለም ደስተኛ ሀገር ሆና የተመረጠች ሲሆን የአለም የደስታ ሪፖርት ደረጃ የሰራዉ ፎርብስ በሰበሰበዉ ድምጽ የህይወት ጥራት ደረጃን ግምገማ መነሻ ማድረጉን ገልጿል፡፡
ከመመዘኛ ነጥቦቹ መካከል ጤናማ የህይወት ዘመን፣ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት በነፍስ ወከፍ ደረጃ፣ ማህበራዊ ድጋፍ፣ ዝቅተኛ ሙስና፣ በማህበረሰብ ውስጥ ያለ ልግስና እና ቁልፍ የህይወት ውሳኔዎችን የማድረግ ነፃነት ናቸዉ፡፡
በዝርዝሩ አሜሪካና ጀርመን 15ኛ እና 16ኛ እንዲሁም እንግሊዝ 19ኛ ደረጃን አግኝተዋል፡፡
በዝርዝሩ ደስተኛ ተብለዉ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃ የያዙት ፊላንድ፣ ዴንማርክ፣ አይስላንድ፣ እስራኤልና ኔዘርላንድ ሲሆኑ ስዊዲን፣ ኖርዌይ ፣ ስዊዘርላንድ ፣ሉክዘንበርግና ኒዉዝላንድ እስከ አስረኛ ያለዉን ደረጃ ይዘዋል፡፡
በዝርዝሩ ደስታ ርቋቸዋል ከተባሉ 20 የዓለም ሀገራት ዉስጥ 15ቱ ከአፍሪካ ናቸዉ፡፡
በዚህም መሰረት ከ20 የዓለም ሀገራት አፍጋኒስታን በ1ኛ ደረጃ ስትቀመጥ፣ ሊባኖስ ፣ ሴራሊዮን፣ ዚምባብዌና ኮንጎ እስከ 5ኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡
ኢትዮጲያ በዓለም ደስታ ከራቃቸው ዝርዝር ዉስጥ በ14ኛ ደረጃ ስትቀመጥ ግብጽ በዚሁ ዝርዝር በ17ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን አመልክቷል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post