የ30 ሚልዮን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ለኮምቦልቻ ሆስፒታል ድጋፍ ተደረገ በኡስታዝ አቡበከር አሕመድ አስተባባሪነት የሙስሊም ኤድ አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚ…

የ30 ሚልዮን ብር የሕክምና ቁሳቁስ ለኮምቦልቻ ሆስፒታል ድጋፍ ተደረገ በኡስታዝ አቡበከር አሕመድ አስተባባሪነት የሙስሊም ኤድ አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ። ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በድጋፍ ርክክቡ ላይ የኮምቦልቻ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ከበደ ይመር ድጋፉ ሆስፒታሉ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል ነዉ ብለዋል። የድጋፉ አስተባባሪ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ የተደረገው ድጋፍ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የሙስሊም ኤድ አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ ቀደም በአላባ እና አፋር ተመሳሳይ ድጋፎችን ማድረጉን አስታውሰዋል። ድርጅቱ በሀገሪቱ የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ የራሱን አስተዋፅኦ ለማበርከት ቀጣይነት ያለው ድጋፎችን እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply