የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መጽሀፍ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ ወጥቷል ተብሎ የተሠራጨው የሃሰት መረጃ መሆኑ ተገልጿል።አዲሱ የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሃፍ ገፅ 18 ላይ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Lv89z4RtN0-WHOhlFg9aba_8wTx6IcEzJ1wCen1z935Qm7bPqeq4ofi_fMZLIiKPj9yC2g2Mik2YoMY38BSr57mAdb01RwsseW4Yj-NMbRr3Uhd9cntHnIChIRMiz6Jy8BOzO89uij0nqCSXojz9EAJxafMGFb1FKad6T6ylrKR1x0qMt_z-7MTEE8odUjrFLdPTZzVudxKWIh39S22m5ixBZbZgmom9UtfFIEppaP8Lq4qCxTNMK0yuW0Aim03TiY2nDzdGubvQgsQiBbImWPn5QowfdXjqzpkSPPeeG2MAu9L9rLOeysITH_xwNaWDU3kkTE6tiABqDL_CWvZuXA.jpg

የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መጽሀፍ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ ወጥቷል ተብሎ የተሠራጨው የሃሰት መረጃ መሆኑ ተገልጿል።

አዲሱ የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሃፍ ገፅ 18 ላይ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ ወጥቷል ተብሎ የተገለፀው ሃሳብ በመፅሃፉ ውስጥ የማይገኝና ሆነ ተብሎ የሃሰት መረጃ መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ያዘጋጃቸውን አዳዲስ የመማርያ መፅሃፍት በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉንና እነኚህምን መፅሃፍቶች በይፋ ርክክብ መፈፀሙ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን በዛሬው እለት በአንዳንድ አካላት በ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሃፍ ላይ አለ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው ፅሁፍ በመፅሃፉ ላይ የማይገኝና የተሳሳተ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው እንዳስታወቀው ዛሬ ይፋ በተደረገውና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ባዘጋጀው የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሃፍ ገፅ 18 ላይ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ ወጥቷል ተብሎ የተገለፀው ሃሳብ በመፅሃፉ ውስጥ የማይገኝና ሆነ ተብሎ የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ውዥንብር ሊፈጥሩ በሚፈልጉ አካላት የተፈበረከ መሆኑን ገልፆ ይህንንም በዛሬው እለት መምህራኑ ራሳቸው በምረቃው ስነስርዓት ላይ ማረጋገጣቸውን ቢሮው አስታውቋል፡፡

እነኚህ አዳዲስ መፅሃፍት ከትምህርት መጀመር ቀደም ብሎ ህትመቱ ተጠናቆ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሰራጩ ያሉ መሆኑንና ህብረተሰቡም ከእንዲህ አይነት የተሳሳቱ ውዥንብሮች ራሱን እንዲጠብቅ ቢሮው በዚህ አጋጣሚ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

የከንቲባ ጽህፈት ቤት

መስከረም 07 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply