የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29 እንደሚሰጥ ተገለፀ

ዕረቡ ሰኔ 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የ2014 የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 29 ቀን 2014 ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በ2014 በከተማ አስተዳደሩ በ179 የመፈተኛ ጣቢያዎች 71 ሺህ 832 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱና ለኹሉም ተማሪዎች አድሚሽን ካርድ መታደሉንም ገልጿል።

ዘንድሮ በኹሉም የፈተና ጣቢያዎች 1 ሺህ 800 ፈታኝ፣ 450 ሱፐር ቫይዘር፣ 179 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን ጨምሮ፤ በድምሩ 2 ሺህ 429 የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በተጨማሪም ከቢሮ ጀምሮ እስከ ፈተና ጣቢያዎች ድረስ የፈተናውን ሂደት የሚከታተል ኮማንድ ፖስት መዋቀሩም ተገልጻል፡፡

ሰኔ 24 ቀንም ለኹሉም ፈተናውን ለሚመለከት የትምህርት ማህበረሰብ ኦረንቴሽን እንደሚሰጥም ተነግሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply