የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ

ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63 ነጥብ 9 በመቶ ያህሉ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል

ሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆነ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት ዓመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ገልጿል።

ለውጤቱ መመዝገብም የኹሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2014 ጀምሮ በኦላይን መመልከት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የዌብሳይቱን አድራሻ ከጥቂት ሰዓታ በኋላ እንደሚያሳውቅም ቢሮው ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply