የG7 እና  የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት “የተፈናቀሉ ዜጎችን በስርዓት፣ በአስተማማኝ እና በፍቃደኝነት ለመመለስ ወሳኝ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት በCoHA በተደነገገው መሰረት የፖለቲካ_ውይ…

የG7 እና  የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት “የተፈናቀሉ ዜጎችን በስርዓት፣ በአስተማማኝ እና በፍቃደኝነት ለመመለስ ወሳኝ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት በCoHA በተደነገገው መሰረት የፖለቲካ_ውይይት መጀመሩን እንደሚቀበል አሳውቋል

የካናዳ፣ የአውሮፓ ህብረት፣  ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ኢጣሊያ፣ ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ የሚስዮን ተልእኮዎች በፕሪቶሪያ የጦርነት ማቆም ስምምነት ትግበራ ላይ የመጀመሪያውን ስትራቴጂያዊ ስብሰባ ካጠናቀቁ በኋላ የጋራ መግለጫ አወጥተዋል።

በመግለጫቸውም የG7 እና  የአውሮፓ ህብረት  አባላቱ ቁልፍ ነጥቦችን  ብለው ካስቀመጧቸው መካከልም ።

-የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ለማፍረስ እና መልሶ ለማዋሃድ ግብአቶችን ለማፋጠን እና  ጥሩውን አካባቢ ለመፍጠር ተጨማሪ እድገት እንደሚያስፈልግ ።

– በግጭቱ የተጎዱትን  የመልሶ ግንባታን ጨምሮ የሚያስፈልጋቸውን የመፍታት አጣዳፊነት እውቅና እንዲሰጡ

– ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር የፍትህ ሂደት እና ተጠያቂነትን ለማራመድ  እንዲሁም የአፈፃፀም ሂደትን ለመገምገም ተዋዋይ ወገኖች መገናኘታቸውን እንዲቀጥሉ  መግፉት።

– የተፈናቀሉ ዜጎች በሥርዓት፣ በአስተማማኝ እና በፈቃደኝነት ለመመለስ ወሳኝ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት በCoHA ድንጋጌዎች መሠረት የፖለቲካ ውይይት መጀመሩን ቅቡልነት መስጠት።

– የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ጊዜያዊ ክልላዊ መስተዳድር  ዘላቂ ሰላም እንዲያገኝ  ማድረግ።

-በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በተከሰቱት ቀውሶች የተሳተፉ ወገኖችም ለንግግር ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርበዋል።

– የአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ የማረጋገጫ እና ተገዢነት ተልዕኮ እንዲስፋፋ እና እንዲራዘም ማበረታታት ናቸው

በለአለም አሰፋ

Source: Link to the Post

Leave a Reply