ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በፀጥታ ችግር ምክንያት ለመስራት ተቸግሪያለሁ አለኩባንያው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ፣ በሀገሪቱ የሚስስተዋሉት ግጭቶች በንግድ እንቅክስቃሴው ላይ ችግር እየፈጠሩብኝ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/GSH_p3snoPqat3SAvUDPbduIXEPFLG0rMGDKJI6960s_OkXO5Airf_pCEFgGhsGFStxs55U3fvK73k_pW-4tETO5MRTWGTfutPI8lE-TuEEX9pmeApQcBzyv-XNW-VzCWg-mG11buWsB2xfBicefvrQGouKFHjD-e6DW0xMMwSqPHdVH7ACBuszntRZfhroIqMSDwxl3IVnkv6afIBIb4mAvWKgbo-p4jJnWFq4kOntxdnVzAdaR0CZpbpvLhtUMfvkd30AK2rpTWmqYUC06yz-ehUsDb8fXNGvU_ePmWLBXEGVNp83__S6sBn1kr6adsmj3JBnfFuyeNTw9qeJKtg.jpg

ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በፀጥታ ችግር ምክንያት ለመስራት ተቸግሪያለሁ አለ

ኩባንያው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ፣ በሀገሪቱ የሚስ
ስተዋሉት ግጭቶች በንግድ እንቅክስቃሴው ላይ ችግር እየፈጠሩብኝ ነው ብሏል።

ዩኒሊቨር ኩባንያ የንፅህና መጠበቂያዎችን፣ ምግብ ነክ ምርቶችን በማምረት የሚታወቅ ሲሆን ከሰባት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ  ኢንዱስትሪ ዞን ወደስራ የገባ ተቋም ነው ተብሏል ።

የዩኒሊቨር ኢትዮጵያ የኮርፖሬት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ደግ ሰው አማኖ ኩባንያቸው ባለው የሰላምና ፀጥታ ችግር ምክንያት ቀላል የማይባል ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ ከሰባት ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን ጠቁመው፤ በቀጣይም የጀመሩትን ሥራ ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

ይሁን እንጅ ድርጅቱ በይበልጥ አቅሙን አሟጦ ስራውን እንዳይሰራ የፀጥታው ሁኔታ ችግር እንደፈጠረበት አንስተዋል ።

በተጨማሪም የታክስ ፖሊሲ ችግር፣የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በይበልጥ እንዳይሰራ አድርጎታል ብለዋል።

ከቦታ ቦታ በፃነት ተዘዋውረው መስራት፤ ምርትን በተገቢው ሰዓት ለፈላጊዎቹ ማድረስና ማከፋፈል አለመቻላየው የዋጋ ጭማሬ ለማድረግ እንደተገደዱም ሰምተናል ።

ልዑል ወልዴ
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply