«ዩኒቨርሲቲው በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው» እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡ሰሞኑን በአንዳንድ የማህራዊ ትስስር ገጾች «…

«ዩኒቨርሲቲው በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው» እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው ሲል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

ሰሞኑን በአንዳንድ የማህራዊ ትስስር ገጾች «ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋ በየቀኑ ከመጨመር ጋር በተያየዘ ለተማሪዎች ምግብ ለማቅረብ ተቸግሯል፡
የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ማሻሻያ አድርጓል» በማለት እየተሰራጨ ያለውን መረጃ በተመለከተ ለጣብያችን መግለጫ ልኳል፡፡

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እንደተቋም የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት በተመለከተ ከዚህ ቀደምም ቢሆን በየወቅቱ እና እንዳስፈላጊነቱ «የምግብ ሜኑ ማሻሻያ» ሲያደርግ ቆይቷል የሚለው መግለጫው፡፡

ይሁን እንጂ ከሰሞኑን አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት ዩኒቨርሲቲው ያደረገውን የምግብ ማሻሻያ ሜኑ አስመልክቶ ተጨባጭነት የሌለውን መረጃ ተሰራጭቶብኛል ሲል በመገለጫው ገልፃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችን ምገባ በተመለከተ ከወራት በፊት የተደረገ የሜኑ ማሻሻያ ለማሳወቅ ማስታወቂያ ያወጣ ሲሆን፤ ይህም የቀን ስህተት የነበረበት መሆኑን እና “አዲስ የተደረገ የሚኑ ለውጥ እንደሌለ እንገልጻለን።

ኃላፊነት በማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት «ዩኒቨርሲቲው በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው» እየተባለ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ ነው ለጣብያችን በላከው መግለጫ ገልፃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቹ ወቅቱ በሚፈቅደው አግባብ ጥራቱን የጠበቀ ምግብ ለማቅረብ የሜኑ ማሻሻያ ከማድረግ ያለፈ በተማሪ ምገባ ላይ አንዳች ጉዳት አይፈጽምም ሲልም አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ገጽታ ማጠልሸት ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፤ ካልሆነ ግን በህግ አግባብ ተጠያቂ የምናደርግ መሆኑን ዛሬ ለጣብችን በላከው መግለጫ አሳውቋል፡፡

ጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከሰሞኑ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ተለጠፈ የተባለ የተማረዎች የምግብ በጀት ሙሉ በሙሉ ከተጠናቀቀ ወራትን አስቆጥሯል የሚል ማስታወቂያ መመልከታችን በመግለፅ ዘገባ መስራታችን ይታወቃል፡፡

ከዛም ባለፈ ዩኒቨርሲቲው የስም ማጥፋት ደረሰብኝ ይበል እንጂ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሶቲው ከፍተኛ የምግብ አቅርቦት ችግር እንዳጋጠመው ለጣብያችን መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply