ዩናይትድ ስቴትስና ሩሲያ በደህንነት ጉዳይ ይነጋገራሉ 

ዩናይትድ ስቴትስና ሩሲያ በሚቀጥለው ጥር ወር በኒዪክሌር የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እና በሩሲያና ዩክሬን ድንበር በሰፈረው ውጥረት ሳቢያ እንደሚነጋገሩ ተገለጸ፡፡

በዋይት ኃውስ የብሄራዊ ጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ዛሬ ለጋዜኞች በሰጡት ማብራሪያ ሁለቱ አገሮች የፊታችን ጥር 2 ተገናኝተው በደህንነት ጉዳይ እንደሚነጋገሩ ገልጸዋል፡፡ 

የሩሲያና የኔቶ ንግግርም ጥር 4 እና 5/2014 የሚካሄድ መሆኑ ተመልከቷል፡፡

ይሁን እንጂ በዩናይትድ ስቴትስና በሩሲያው ውይይት ላይ የዩክሬንን ጉዳይ አስመልከቶ ለዩክሬን ነጻነትና ጥቅም ሲባል በሁለቱ አገሮች ከውሳኔ የሚደርሰበት ምንም ዓይነት ውይይት እንደማይደረግ ቃል አቀባዩ አመልክተዋል፡፡ 

ዩክሬንን በተመለከተ የፕሬዚዳንት ባይደን አቋም ግልጽና ያልተለወጠ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ከተባባሪዎችዋ የኔቶ አባላት ጋር ተግባራዊ በሚደረግ ሁለቱ የማእቀብና ዲፕሎማሲ መንገድ የሚፈጸም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

ሩሲያም በአንጻሩ ኔቶ ወደ ሩሲያ ድንበርና አካባቢዋ የሚያደርገውን መስፋፋት የሚያቆም መሆኑን ዋስትና ሊሰጠኝ ይገባልየሚል አቋም መያዟ ተመልከቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply