ዩናይትድ ስቴትስን እና አጋሮቿን ሩሲያን ለሃገራት “የተለየ የመናገድ ዕድል” ከሚያሰጠው ዝርዝር ሊሰርዙ ነው

https://gdb.voanews.com/023a0000-0aff-0242-10bf-08da037ac220_w800_h450.jpg

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአውሮፓ ህብረት እና የሰባቱ ሀገራት ቡድን ጋር በመሆን አገራቸው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረገችው ወረራ የተነሳ በዓለም የንግድ ማህበር “የተለየ የመናገድ ዕድል” ከሚያሰጠው የሃገሮች ዝርዝር እንድትሰረዝ የሚያደርገውን ውሳኔ ዛሬ ይፋ ሊያደርጉ ነው።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እና ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጭ እንዳመለከቱት እርምጃው ዩናይትድ ስቴትስን እና አጋሮቿን ሩሲያ ከውጭ በምታስገባቸው ሸቀጦች እና ምርቶች ላይ ቀረጥ እንዲጥሉባት የሚያስችል ነው።

ይህ የባይደን እርምጃ የመጣው ከሩሲያ ጋር ያለውን “ቋሚ እና መደበኛ የንግድ ግንኙነት” በመባል ከሚታወቀው አሰራር እንድትፋቅ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቱ የሁለቱም ፓርቲዎች በጋራ ያደረጉትን ግፊት ተከትሎ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply