ዩናይትድ ስቴትስ ህወሓትን አበረታታ እንደማታውቅ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ አስታወቀ

“ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ ዩናይትድ ስቴትስ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም” ሲል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ አስታውቋል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ባለፈው ሣምንት በትግራይ ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ስለሰጡት አስተያየት መሥሪያ ቤቱ ተጠይቆ ለቪኦኤ በሰጠው ምላሽ ነው ይህንን የገለፀው።

በሌላ በኩል የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ “እጅግ ብርቱ” ያላቸው “አማራና አፋር ክልሎች ውስጥ እንደተፈፀሙ የተነገረ የመብቶች ጥሰቶች፣ የጭካኔ አድራጎቶችና የውድመት ውንጀላዎች ግልፅ ምርመራ እንዲካሄድባቸው” አሳስቧል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply