ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ባለሥልጣናት ላይ የተጣለውን የጉዞ እቀባ አሰፋች

https://gdb.voanews.com/023d0000-0aff-0242-10a8-08da0bfd4909_w800_h450.jpg

የባይደን አስተዳዳደር በቻይና ባለሥልጣናት ላይ የጣለውን የጉዞ እቀባ በማስፋት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የብሄረሰቦችና የሃይማኖት ተከታዮችን በመጨንቆ በተከተሰሰሱ ባለሥልጣናት ላይ የጉዞ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ሰኞ ባወጣው መግለጫ ማዕቀቡ የሚያነጣጥረው የተወሰኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የንግግርና የእምነት ነጻነት በማፈን ተጠያቂ የሆኑ የቻይና ባለሥልጣናት ላይ መሆኑን ገልፆ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲመጡ አይፈቀድላችውም ብሏል፡፡

ሚኒስቴሩ እቀባው የተጣለባቸው ባለሥልጣናት የትኞቹ እንደሆነ በዝርዝር አላመለከተም፡፡

የጉዞ እቀባው ቀደም ሲል የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቻይና ኡግር ሙስሊሞችን በመጨቆን፣ እንዲሁም በሆንግ ኮንግ የዴሞክራሲ ተሟጋች አክቲቪስቶችን በማፈን በተከሰሱት የቻይና ባለሥልጣናት ላይ ከጣሉት የቪዛ ማዕቀብ በተጨማሪ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply