ዩናይትድ ኪንግደም የኤርትራው አምባሳደር ከአገሯ ለቀው እንዲወጡ አዘዘችየዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በለንደን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት እስጢፋኖስ ሃብተማርያም ከአገሩ እንዲወጡ ማዘዙን ዲ…

ዩናይትድ ኪንግደም የኤርትራው አምባሳደር ከአገሯ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት በለንደን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት እስጢፋኖስ ሃብተማርያም ከአገሩ እንዲወጡ ማዘዙን ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደነገሩት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ኤርትራ እና ዩናይትድ ኪንግደም የአምባሳደሩን መባረርን በተመለከተ በይፋ የሰጡት መግለጫ የለም።

በአሁኑ ወቅት በለንደን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ድረ-ገጽ እንደሚያመለክተው የአምባሳደሩን ቦታ በመሸፈን የኤምባሲው (ሚሲዮን) ከፍተኛ ተጠሪ በመሆን የሚሠሩት ሳሌህ አብዱላህ ናቸው።

የዩኬ መንግሥት አምባሳደር እስጢፋኖስ ሃብተማርያም ላይ ከአገር እንዲወጡ የወሰደው እርምጃ፣ ኤርትራ ቀደም ብሎ ለወሰደችው ተመሳሳይ ውሳኔ ምላሽ መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት በኤርትራ የዩኬ አምባሳደር የሆነው የተሰየሙት ዲፕሎማት በኤርትራ መንግሥት አስፈላጊውን ዲፕሎማሲያዊ ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ወደ አሥመራ መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል።

ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply