ዩናጋንዳ 15 ሰዎችን በሽብርተኝነት ከሰሰች

ዩጋንዳ የሽብር ጥቃት በማድረስና ከሽብርተኞ ጋር ተባባሪ ሆነዋል በሚል 15 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቷን ትናንት አስታወቀች፡፡ 

ተከሳሾቹ የተከሰሱት ባለፈው ጥቅምትና ህዳር ወር ውስጥ በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ቢያንስ ለስድስት ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል በተባሉ የቦምብ ፍንዳታዎች ተጠርጥረው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ለቦምብ ጥቃቶቹ ከእስላማዊ መንግሥት አራማጅ ተዋጊዎች ጋር ግንኙነት አለው የተባለው የተባበሩት ዲሞክሲያ ኃይሎች ግንባር ኃላፊነቱን መውሰዱ ይታወቃል፡፡ 

ለብዙ ሰላማዊ ሰዎች ሞት ተጠያቂ ነው የተባለውን ይህን ድርጅት ኡጋንዳና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኃይሎች በጋራ ሆነው ኮንጎ ውስጥ እየወጉት መሆኑ ይታወቃል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply