ዩክሬን ምዕራባዊያን አሁንም የጦር መሳሪያ እንዲያቀርቡላት እየተማጸነች ነው፡፡የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ የአውሮፓ ህብረት የጦር ጄቶች እና ሚሳኤሎች እንዲሰጣት ካልሆነ ግን ረጅም ጦርነ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/P3gy1f4c_kQeqn6nzIxphk4gVJM88ZhZsLmwZnGhttKG0jK-by_9t9WapbD_e2b8EQ9At-j6ACmwu9Xd6kK8lQ2eoWMCULbiQKuKhe-KV4DqROM_OpP9hZhNenOj6VKUD2m_4eqFsccaRuOpFXzrEWu1fMBUTvTGk-O6p--ZeukUumB66YtI8mb5cWPnb-gQgXDn68x8scTtAM6KUh3VRfvtc4U-ENZxp-UDWzKAmKppA1dZ6zwZTtt8jHl2hVVAUe_Rs7Gc6XEQwD0yz_3lfYe7sXHMdJ9oN8C1DbQIo8kh4fuww9a2ClKU8FOaNLviCeZ34wCBvkbOrKfuarSPKQ.jpg

ዩክሬን ምዕራባዊያን አሁንም የጦር መሳሪያ እንዲያቀርቡላት እየተማጸነች ነው፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ የአውሮፓ ህብረት የጦር ጄቶች እና ሚሳኤሎች እንዲሰጣት ካልሆነ ግን ረጅም ጦርነት ጠብቁ ብለዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ለዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች አስፈላጊነት የሰጡት አስተያየት በአውሮፓ ህብረት መሪዎች ዘንድ አልተወደደላቸውም፡፡

ፕሬዝዳንቱ የአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የሚያደርጉትን ድጋፍ በፍጥነት እንዲጨምሩላቸው የጠየቁ ሲሆን፣ በተለይም ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል እና የጦር ጀቶች እንዲያቀርቡላቸው፤ይህ ካልሆነ ግን ጦርነቱ ለረጅም ጊዜ መካሄዱ አይቀሬ እንደሆነ አስረግጠው ገልጸዋል፡፡

አንድ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣን በብራስልስ በቪዲዮ በተደረገ ቆይታ ዘሌንስኪ በደቡባዊ ዩክሬን እና ምስራቃዊ የሃገሪቱ ክፍል የጦር ግንባር አቅራቢያ በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን ለሶስተኛ ጊዜ ጎብኝተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የጀመረችውን ወረራ ወደ ሁለተኛው ዓመት እየገባች ባለችበት ወቅት፣ ሩሲያን ለመቆጣጠር እርምጃ ለመውሰድ የአውሮፓ ህብረት የሄደበትን ዳተኝነት ተችተዋል።

ዘሌንስኪ እንዳሉት የረዥም ርቀት የጦር መሣሪያዎችን እና ዘመናዊ ተዋጊ ጀቶችን ለማቅረብም ሆነ ሃገራቸውን የአውሮፓ ህብረት አባል ለማድረግ ሂደቱን ያዘገየው የአውሮፓ ህብረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን

Source: Link to the Post

Leave a Reply