ዩክሬን ቆሻሻዉን ቦምብ ልትጠቀም ነዉ በሚል ከሞስኮ የቀረበባትን ዉንጀላ ምእራባዉያኑ ዉድቅ አደረጉ፡፡ምዕረባዉያን ሩሲያ ዩክሬንን በመወንጀል አዉዳሚ የጦር መሳሪያ እንዳትቀምም አስቀድመዉ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/esDqPv6isdzlG30a6b36zVyBFk4KpUEOqulejdx9osfROwgwdvj_AgQg8o1F3dabVcwFvNJlINgxsa_yoWQhkJzgXETupPGALEDYcfwuipnuWZ6rgN4XOYA1u0R9p-FwaGGyzVNw8xCW809zA9pHhkCmStYp2QoP1D_7AtGov2uNDFh-pF2glFuA1oCTg-sKyC3GxlIMfwPpqnC0uJDPod36Wt_bir6lSOpHBqFvSuBnt1TSrQgNdLO-AtDxEJ_r0dRmC1ApXGxmU-LzuKs1EehEkGXwYRJSyqSZcR1u8K723fJ8ClbvSZE3rZ0CCvRU_bmY9LBwZNPBpVddQQ2h1g.jpg

ዩክሬን ቆሻሻዉን ቦምብ ልትጠቀም ነዉ በሚል ከሞስኮ የቀረበባትን ዉንጀላ ምእራባዉያኑ ዉድቅ አደረጉ፡፡

ምዕረባዉያን ሩሲያ ዩክሬንን በመወንጀል አዉዳሚ የጦር መሳሪያ እንዳትቀምም አስቀድመዉ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሞስኮ ቆሻሻዉን ቦምብ ልትጠቀም ትችላለች በሚል ዩክሬን ላይ ክሰ ማቅረቧን ተከትሎ፣ ምዕራባዉያኑ ሩሲያ እራሷ ልትጠቀም አስባ ነዉ በሚል ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነዉ፡፡

አሜሪካ ለእንግሊዝና ፈረንሳይ፣ የፑቲን ጦር ከጠብ አጫሪነቱ እንዲታቀብ አሳስበዋል፡፡

ዩክሬን ሩሲያን በቆሻሻዉ ቦምብ ለመምታት እየተዘጋጀች እንደምትገኝ የሞስኮ የወታደራዊ አመራሮች መናገራቸዉን አልጄዚራ ነዉ ያስነበበዉ፡፡
ይሁን እንጅ ምእራባዉያኑ የሞስኮን ዉንጀላ መሰረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለዉታል፡፡
በተጨማሪም አገራቱ ለዩክሬን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ በመናገር ላይ ናቸዉ፡፡

ከትናንት በስትያ የሩሲያ ወታደራዊ አመራሮች ከአሜሪካ አቻቸዉ ጋር መወያየታቸዉ መገለጹ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ

ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን
ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply