ዩክሬን በሩሲያ ላይ የተቀናጀ የድሮን ጥቃት ዘመቻ ልትጀምር መሆኑን አስታወቀች::የዩክሬን ጦር በቀጣይ ጊዚያት ትኩረቱን በድሮን ጥቃት ላይ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡የሀገሪቱን የአየር…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/UeHZ4aSCgam9JkeYEUgWYgx-vAvgKpnyvH6tOdEvSBv6wRjyquJqWNSoG1sLODPNWNqljGtV3sSkUlCTtzvHtk1xd0YG4hUpm1ET7kOADwZphUx0Xh0H4hf52YhFSLxG2AFrYLctaqaKTFAOcFsZ0RK5v7kMr1Brr1L2aADa3KtgOsBOjA1x8oRD5RIOMjOqXjUcAHZrUlnd3omc9GzBaYoUoVToGQauh2MBWYucYwUGQC4Iy7iqUBAfYe0RkPZWwWrrTaG2QGc7ZAG_pQaQBl1-XrKu28cAL9NBFXpiyUY0uukodugrdrr74zLyhYFRdhZjnJa2JRn-nXkyU5RqLg.jpg

ዩክሬን በሩሲያ ላይ የተቀናጀ የድሮን ጥቃት ዘመቻ ልትጀምር መሆኑን አስታወቀች::

የዩክሬን ጦር በቀጣይ ጊዚያት ትኩረቱን በድሮን ጥቃት ላይ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡

የሀገሪቱን የአየር ኃይል እየመሩ የሚገኙት ሰርጌ ብራኖቭ ሞስኮ ላይ ከፍተኛ ዉድመት የሚያደርስ የድሮን ጥቃት እንከፍታለን ነዉ ያሉት፡፡

ጦሩ ኢላማ አድርጎ ከሚንቀሳቀስባቸዉ የሩሲያ አካባቢዎች መካከል ክሪሚያ ቀዳሚዋ አንደምትሆንም ይፋ አድርጓል፡፡

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ኬይቭ በሩሲያ ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶችን እየወሰደች እንደምትገኝም አርቲ ኒዉስ ዘግቧ፡፡

በአካባቢዉ ያለዉ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ የምድር ጦሩን በፈለገዉ ደረጃ ወደፊት እንዳያጠቃ ስላደረገዉ ዩክሬን የድሮን ጥቃትን አማራጭ እንዳደረገች በዘገባዉ ሰፍሯል፡፡

የሩሲያ ባለስልጣናት በበኩላቸዉ ዩክሬን እየወሰደች ያለችዉ የድሮን ጥቃት በንጹሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ነዉ በሚል እከሰሰች ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ

ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply