ዩክሬን በብራስልስ የተሰበሰቡት የኔቶ መሪዎች ተጨማሪ እርዳታ እንዲሰጧት ጠየቅች

https://gdb.voanews.com/093e0000-0a00-0242-0cc9-08da0d821bd9_w800_h450.jpg

የኔቶ አባል አገራት አንድ ወር ላስቆጠረው የሩሲያው የዩክሬን ወረራ የአጭርና የረጅም ጊዜ ምላሽ ለመስጠት በብራስል ተገናኝተው እየመከሩ ነው፡፡ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪም በቀጥታ ለመሪዎቹ የሚያቀርቡትን ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያቀርቡም ተመልክቷል፡፡

ስብሰባው ከመካሄዱ በፊት ዘለንስኪ ለኔቶ አባላት አገራት በእንግዝሊኛ ቋንቋ ባስተላለፉት የቪድዮ መልዕክት ለዩክሬን ኃይሎች የጦር መሣሪያን ጨምሮ “ውጤታማና ያልተገደበ” ድጋፋቸውን እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

ዘለንስኪ በመላው ዓለም የሚገኙ ህዝቦች የሩሲያን ውግዘት ወደ አደባባዮቻቸው እየወጡ እንዲቃወሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

“የዩክሬን ምልክቶችን በመያዝ፣ ለነጻነትና ለህይወት ድጋፋችሁን ለመስጠት ወደ የአደባባዮቻችሁ ወደ የጎዳናዎቻችሁ ውጡ! እንድትታዩና እንድተስሙ ሁኑ” ብለዋል፡፡ 

ከኔቶ ምክክር በተጨማሪ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ሀሙስ ከቡድን 7 መሪዎችና ከአውሮፓ ምክር ቤት ጋር ይነጋገራሉ፡፡ 

የብሄራዊ ደህንነት አማካሪው ጄክ ሱሌቫን አጠቃላይ ግቡ “ባለፈ ወር ውስጥ ያየነው መፍትሄና አንድነት አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ዘላቂ እንዲሆን ማድረግ ነው” ብለዋል፡፡

ሱሌቫን፣ ይህ ደግሞ አገሮች ለዩክሬን የሚሰጡትን የመሳሪያ እርዳታ ጨምሮ፣ በሩሲያ ላይ ያለውን ማእቀብ ተግባራዊ እንዲያደርጉና በግጭቱ ተጎጂ ለሆኑት የሚሰጡትን የሰብአዊ እርዳታ ያካትታል ብለዋል፡፡ 

ባይደን በሩሲያ አገዛዝ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና የፖለቲካ ሰዎች፣ የአገዛዙ ከበርቴዎችና ሌሌች ተቋማት ላይ ያነጣጠረ አዲስና ተጨማሪ ማዕቀብ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ብሪታኒያ በተመሳሳይ ተጨማሪና አዳዲስ ማዕቀቦችን የምትጥል መሆኑን ገልጻለች፡፡

ቻይና በሩሲያ ላይ የሚጣለውን ማዕቀብና የፕሬዚዳንት ባይደንን ማስጠንቀቂያ የነቀፈች ሲሆን፣ ይህ ሩሲያ በመወሰድ ላይ የምትገኘውን እርምጃ እንድታሻሽል የሚረዳት አይደለም ብላለች፡፡ 

የኔቶ ዋና ጸሀፊ ሩሲያ በዩክሬን የኬሚካል የጦር መሳሪያ መጠቀሟን ነቅፈው የኔቶ አባል አገራት ዩክሬን ራስዋን ከኬሚካል ከባዮሎጂካል ከሬዲዮሎጂካል እና ኒዩከለርስ ጋር ራሷን እንድትከላከል የመሳሪያ እርዳታ ሊሰጧት ይገባል ብለዋል፡፡ 

የባይደን አስተዳደር ባለሥልጣናት ቀደም ሲሉ በሰጡት መግለጫ ሞስኮ የኬሚካል መሳሪያዎችን ልትጠቀም ትችላለች ሲሉ ያስጠነቀቁ ሲሆን፣ ወረራቸውን ፍትሃዊ ለማድረግ ዩክሬናውያንም ይጠቀማሉ የሚለውን የሀሰት ውንጀላቸውን እንዲያቆሙ ማስጠንቀቃቸው ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንክን ትናንት በሰጡት መግለጫ የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬን የጦር ወንጀል መፈጸማቸውን ጠቅሰው ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያ ተጠያቂ እንድትሆን ትሰራለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሩሲያ የጦር ወንጀል ፈጽማለች የሚለውን ክስ በተደጋጋሚ ስታስተባብል ቆይታለች፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply