ዩክሬን እና ሩሲያ ሶስተኛውን ዙር የሰላም ድርድር ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል ተባለ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2014 ዩክሬን እና ሩሲያ ሶስተኛውን ዙር የሰላም ድርድር ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል ተባለ። ለሁለት ሳምንታት ከሚጠጋ ጦርነት በኋላ ሁለቱ ሀገራት ለሦስተኛው ዙር ድርድር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ የሁለቱ ሀገራት የልዑካን ቡድን አባላት ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በምዕራብ ቤላሩስ በሚገኘው ብሬስት ክልል የሁለት ዙር የሰላም ድርድር ላይ ሲሆን ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ሰላማዊ ዜጎችን ሁኔታ ለማመቻቸት
በማለም ሁለት ከተሞች የሰብአዊ አገልግሎት መስጫ እንዲሆኑ ተስማምተው ነበር፡፡

ይሁን እንጂ አንደኛዋን ከተማ ለመልቀቅ የተደረገው ሙከራ እሁድ እለት ሳይሳካ ቀርቷል ሲሉ ክሬምሊን እና የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቀዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን የሰብአዊ አገልግሎት መስጫ ከተሞች ይሆናሉ ተብለው በተመረጡ ከተሞች የፈፀሙትን የተኩስ አቁም ስምምነት እያከበሩ አይደለም የተባለ ሲሆን ለዚህ አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ ወቀሳ እያቀረቡ ይገኛሉ አልጄዚራ ዘግቧል። የሩሲያ ሃይል በደቡብ በኩል በዩክሬን መዳረሻ በአዞቭ ባህር በኩል መስመሩን ለማቋረጥ ሞክሯልም ተብሏል፡፡ ሞስኮ የሰላማዊ ዜጎች መጠለያ ትሆናለች የተባለችው ማሪዮፖል ከተማን መያዟ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 ወደ ግዛቷ ከቀላቀለቻት ክሬሚያ ጋር የመተላለፊያ መስመር እንድትመሠርት ያስችላታል ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply