ዩክሬን ከ400 በላይ ስፖርተኞች ሞቱብኝ አለች።

በጦርነት ምክንያት እስካሁን ከ400 በላይ ስፖርተኞቼ ሞተውብኛል ስትል ሃገሪቷ አስታውቃለች።

ዩክሬን ; ሩስያ ጦርነት ካወጀችብን ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ 410 ስፖርተኞች ሞተዋል ብላለች።

የዩክሬን የስፖርት ኮሚቴ ባወጣው ሰፊ ሪፖርት መሰረት ለሃገረቸው ክብር ብለው በጦርነቱ የተሳተፊም ያልተሳተፊም 410 ያህል ስፖርተኞች ሞተዋል ሲል አስታውቋል።

ዩክሬን ለህልፈት ተዳርገዋል ካለቻቸው ስፖርተኞች መካከል የቅርጫት ኳስ እና እግር ኳስ ተጫዋቾች እንደዚሁም ራጮች ይገኙበታል ብላለች።

እኛ ዩክሬናዊያን በጦርነቱ ምክንያት የሞቱ ስፖርተኞቻችን የሚገባቸውን ክብር ባንሰጣቸውም ታሪክ ሁሌም ያስታውሳቸዋል ሲል የሃገሪቱ የስፖርት ኮሚቴ ገልጿል።

ስፖርተኞቹ ለሃገራቸው ነጻነት እና ለእውነት መሰዋዕት ሆነዋል ሲልም ገልጿቸዋል።

ከሁለት አመት በላይ ባስቆጠረው የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት እስካሁን ድረስ 18ሺህ ያህል ዜጎች በዩክሬን በኩል መሞታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት መረጃ ያሳያል።

የሁለቱ ሃገራት ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥር 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply