ዩክሬን የሩሲያን ድሮኖች መትታ መጣሏን አስታወቀች

https://gdb.voanews.com/3132af33-459d-48e8-ab0a-13d0d474d818_w800_h450.jpg

ሩሲያ ዛሬ ሌሊቱን ዩክሬን ላይ የአየር ጥቃት አድርሳለች። የዩክሬን ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ሩሲያ የላከቻቸው በርካታ ድሮኖች ዋና ከተማዋን ኪየቭን ጨምሮ የተለያዩ ዒላማዎች ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

የመዲናዋ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት ድሮኖቹ ተመትተው ሲወድቁ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር የዩክሬን የአየር ጥቃት መከላከያዎች በአመዛኙ ከተማዋን ጠብቀዋታል።

ሩሲያ ወደኪቭ አካባቢ አርባ ድሮኖች ልካ እንደነበር የተናገሩት የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ “በሙሉ አውድመናቸዋል” ብለዋል።

ሩሲያ በኢራን በተሰሩ ሻሄድ ድሮኖች በመጠቀም በዩክሬን ከተሞች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ መሆኗ ይታወቃል።

እሁድ ሌሊት ሩሲያ በሰነዘረችው የድሮን ጥቃት የዩክሬን ኃይሎች 45 ድሮኖችን መጣላቸውን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ መናገራቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply