ዩክሬን የውጭ ድጋፍ በመቀነሱ ወታደራዊ ዘመቻዎችን ለማቋረጥ መገደዷን አስታወቀች

ከሩስያ ጋር ጦርነት ላይ ያለችው ዩክሬን ከሌሎች ሀገራት የሚደረግላት ድጋፍ በመቀነሱ ምክንያት የተወሰኑ ወታደራዊ ዘመቻዎችን ለመቀነስ እየተገደደች መሆኑን አስታውቃለች።

የሀገሪቱ ወታደሮች “በሁሉም የውጊያ ግንባር” የተተኳሽ ጥይት እጥረት ስላጋጠማቸው፣ “ትልቅ ችግር” እየተፈጠረ መሆኑን፣ የዩክሬን ከፍተኛ ጄነራል የሆኑት ኦሌክሳንደር ተርና-ቭስኪ ተናግረዋል።

ዩክሬን ይህ ችግር ያጋጠማት ከአሜሪካ እና ከአውሮፓ ህብረት በድጋፍ ልታገኝ የነበረው የቢሊዮኖች ዶላር ድጋፍ በፖለቲካዊ አለመግባባት ምክንያት ተይዞ በመቆየቱ ነው።

ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply