ያለንበት መጋቢት ወር “ፍረጃ ይቁም” በሚል መሪ ቃል የዳውን ሲንድረም ወር ተብሎ እንደሚታሰብ ተገለፀ።

የዘንድሮ የዳውን ሲንድረም ቀን በአለም ለ13ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ9ኛ ጊዜ ፍረጃ ይቁም” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገልጿል።

ወሩን ለማክበርም ፍቅር የኢትዮጵያ አእምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማህበር ፣ ነህያም ኦቲዝም ማእከል ፣ ኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማእከል ፣ ቤተምህረት ሁሉን አቀፍ የልማት ድርጅት እና ብሩህ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች እንክብካቤ እና ትምህርት ማዕከል በጋራ ሆነው ለማክበር ዝግጅታቸውን እዳጠናቀቁ ተናግረዋል።

መጋቢት ወር የዳውን ሲንድረም ወር በመሆኑ የፊታችን እሁድ መጋቢት 8/2016 አመታዊ የእግር ጉዞ እንደሚደረግም አንስተዋል።

መጪው ሚያዝያ ወርም የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ተብሎ እንደሚከበር ተገልጿል።

በየአመቱ የሚያዝያ ወሩ ሙሉ የአለም አቀፍ ኦቲዝም ግንዛቤ ወር ተብሎ በመሰየሙ እጅግ በደመቀ መልኩ በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ እንደሚከበርም ተናግረዋል።

እነዚህ ቀኖች ሲከበሩም ቀኑን ከማክበር ባለፈም የአይምሮ እድገት ውስንነት ስላለባቸው ሰዎች ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በሰፊው ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል።

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply