ያለዕድሜ ጋብቻን ለማስቀረት ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው የሴቶች ንቅናቄ እና ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ስማቸው ዳኘ ለአሀዱ እንዳሉት በአማራ ክልል ያለውን ያለእድሜ ጋብቻ ለማስቀረት በተሰራው ስራ በተያዘው አመት ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡

በ2012 ዓ/ም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋቱን ተከትሎ ትምርት ቤቶች በተዘጉበት ወቅት በክልሉ ያለድሜ ጋብቻ ተስፋፍቶ የነበረ ሲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ባሻገር ድርጊቱን የሚፈፅሙ አካላትን በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በዚህም በ2013 ዓ/ም ጥሩ በሚባል ደረጃ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

ቢሮው ችግሩን ዘላቂ በሚባል ደረጃ ለመቅረፍ የልጃገረዶችን የግንዛቤ አቅም በማሳደግ ለችግሩ ተጋላጭ እንዳይሆኑና ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎሉ የሚያስችላቸውን ስልጠናም ሰጥቻለው ብሏል፡፡

እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውንም በግንዛቤ የማንቃት ስራ መሰራቱን የተናገሩት ዳይሬክተሩ የጎጂ ልማድ ህጋዊ ጥምረት በማቋቋም እየተሰራ ስለመሆኑ ነግረውናል፡፡

ቀን 26/11/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply