ያለፉት ስድስት ዓመታት ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ለሰብዓዊ መብቶች ፈታኝ ግዜ ነበር ሲሉ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን…

ያለፉት ስድስት ዓመታት ለሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ለሰብዓዊ መብቶች ፈታኝ ግዜ ነበር ሲሉ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ በርካታ ለውጦች ተካሂደዋል።
ይሁን እንጂ በተለይም መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች በሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ አላግባብ ተጥሰዋል ሲሉ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት በሀገሪቱ የተስተዋሉ ጦርነቶች በተለይም ሴቶችን፣ህፃናት እና አረጋዋያንን ህይወት እጅጉን አክብዷል፡፡
በርከቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሸሽተዋል፣በርካታ ዜጎች ኗሯቸውን በመጠለያ ጣብያዎች አድርገዋል፡፡
እነዚህ ሁኔታዎች ታድያ በሀገሪቱ ተፈጥሮ የነበረውን ትለቅ ተስፋ እዳጠፋባቸው የሚናገሩ ቀላል አይደሉም፡፡

ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የቪዢን ኢትየጵያን ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ /ቪኮድ/ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ታደለ ደርሰህ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ዙሪያ የታዩ በጎ ጎኖች ነበሩ ይላሉ፡፡
በተለይም አፋኝ የነበሩ ህጎች ከ2010 በኃላ እንዲሻሻሉ መደረጉ ትልቅ እርምጃ መሆኑን ያነሳሉ፡፡
ይሁን እንጂ በአሁን ሰዓት ያለው ሁኔታ በርካታ ነገሮች ካሰቧቸው ውጪ እንደሆነባቸው ይናገራሉ፡፡

ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አለመቻሉ፣የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ፣በየግዜው እየተባባሰ የመጣው ጦርነት፣ሰዎች ያላግባብ መታገት እና ዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች አፋና በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ከጣብያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
ሌላው ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው አቶ ያሬድ ሃይለማርያም የኢትዮያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡

እንደሳቸው ሀሳብም የለውጡ መንግስት የሚባለው አካል ወደ ስልጣን ሲመጣ የሚዲያው እና የፖለቲካ ምህዳሩ ወለል ብሎ መከፈቱ በጣም በጎ ጎን እንደነበር ያነሳሉ፡፡
ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታን አሁን ላይ ቆመው ሲያስቡት የነበረው ሁሉ እንዳልነበር ሆኗል አስብሏቸዋል፡፡

በተለይም ኢትዮጵያ ተመልሳ በጋዜጠኞች እስር ከሰብ ሰሃራን ሀገራት በሶስተኝነት መቀመጧ ምህዳሩ በምን ያህል ፍጥነት መልሶ መጥበቡን የሚያሳይ ነው ሲሉ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ድፍን ስድስት ዓመታቸውን ባለፈው መጋቢት 24 2016 ዓ.ም አክብረዋል፡፡

በነዚህ ስድስት ዓመታት ውስጥ በተለይም ከሰብዓዊ መብቶች አኳያ ኢትዮጵያ በርካታ ተስፎች ሰንቃ የነበረ ቢሆንም በአሁን ሰዓት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ወደ ቀደም ግዜያቶች ወደ ነበሩበት ተምልሷል ሲሉ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ይወቅሳሉ፡፡

በአቤል ደጀኔ

መጋት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply