#ያለ እድሜ ለሚከሰት የቆዳ መሸብሸብ አጋላጭ ሁኔታዎችእድሜ የጨመረ በሄደ ቁጥር ከማይቀሩ የተፈጥሮ ሂደቶች መካከል አንዱ የቆዳ የመሸብሸብ ነው፡፡ቆዳችን በተፈጥሮ የመወጠጥ አቅሙን ይቀንሳል…

#ያለ እድሜ ለሚከሰት የቆዳ መሸብሸብ አጋላጭ ሁኔታዎች

እድሜ የጨመረ በሄደ ቁጥር ከማይቀሩ የተፈጥሮ ሂደቶች መካከል አንዱ የቆዳ የመሸብሸብ ነው፡፡
ቆዳችን በተፈጥሮ የመወጠጥ አቅሙን ይቀንሳል እንዲሁም በቶሎ የሚጎዳም ይሆናል፡፡ ነገር ግን የቆዳ መሸብሸብ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት እንደሚችል በባሞያዎች ዘንድ ይገለጻል፡፡

በቆዳ ላይ የመስመር እና የመኮማተር አይነት ምልክት ሲኖር የቆዳ መሸብሸብ ተከሰተ ሊባል እንደሚቻል ይነገራል፡፡

ከ35 ዓመት በፊት ወይም በ20ዎቹ የእድሜ ክልል ላይ በተፈጥሮ የቆዳ የመወጠር አቅም መቀነስ እና የመሸብሸብ ሁኔታ ካለ ያለ እድሜ የሚመጣ የቆዳ መሸብሸብ እንደሚባል የነገሩን፤ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የቆዳ ሀኪም ዶክተር ስምረት መስፍን ናቸው፡፡

በቆዳ ውስጥ ያለው የኮላጅን ንጥረ ነገር እየቀነሰ ሲሄድ ቆዳ ጥንካሪውን እንዲያጣ እና በተፈጥሮ የመወጠር አቅሙን ሊቀንስ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

#ቆዳ እንዲሸብሸብ እና ጥንካሬውን እዲያጣ ከሚያፋጥኑ ምክንቶች መካከል

• ከፍተኛ ለሆነ የጸሃይ ጨረር ተጋላጭ መሆን
• የአልኮ ይዘት ያላቸውን መጠጦች አዘውትሮ መጠጣት
• በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
• አብዝቶ መጨነቅ
• የእንቅልፍ እጦት
• ቆዳ ለድረቀት ተጋላጭ ከሆን

የቆዳ መሸብሸብ በብዛት የሚስተዋለው በፊት ላይ ሲሆን፤

• ግንባር አከባቢ
• በአይን ስር
• ጉንጭ አከባቢ
• በአንገት አካባቢ
• ከእነዚህ በተጨማሪም በእጅ ላይ የቀዳ መሸብሸብ የሚስተዋል ይሆናል ተብሏል፡፡

#ያለ እድሜ የሚመጣ የቆዳ መሸብሸብን ለመከላከል

• ሲጋራን ማጨስን ማስወገድ

• እንደ ዣንጥላ፣ ኮፍያ በመጠቀም ከቀጥታ የጸሃይ ጨረር ተጋላጭነት መቀነስ
• በተቻለ አቅም ጭንቀትን ለመቀነስ መሞከር
• ጥሩ እንቅልፍ መተኛት
• በቂ ፈሳሽ መውሰድ እና ከ1.5 እስከ 2ሌትር ውሃ መጠጣት
• የተመጣጠነ አመጋገብን መከተል አትክልት አና ፍራፍሬን በእለት ምግብ ላይ ማዘጋጀት
• ስር የሰደዱ የሚያስጨንቁ ችግሮች ካሉ ለመፍታት መሞከር ያለጊዜው የሚከሰት የቆዳ መሸብሸብን ለመከላከል በዘርፉ ባለሞያዎች ዘንድ የሚመከር ነው፡፡

ሰዎች በፊት ከሚያከውኗቸው ገለጻዎች ለምሳሌ መኮሳተር፣ መገረም እና ሌሎችን አለማዘውተር፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ልማዶች ፊት መስመር ይዞ እንዲቆይ እና መሸብሸብን ሊያስከትል በመቻሉ መሆኑ ይገለጻል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው
ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply