ያላባራው የመተከል ወገናችን ሞት! ጋዘጠኛ ያለለት ወንድዬ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዛሬ በቀን 25-04-2013…

ያላባራው የመተከል ወገናችን ሞት! ጋዘጠኛ ያለለት ወንድዬ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዛሬ በቀን 25-04-2013 ዓ.ም በማንዱራ ወረዳ በኤዲዳ ቀበሌ ከቀኑ 11:00 ሰዓት አካባቢ ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ በመጓዝ ላይ ባለ መኪና የተደራጁ የጉሙዝ ወጣቶች በተኮሱት ጥይት አንድ ሰው ህይወቱ ሲያልፍ ሁለት ቆስለዋል። ህይወታቸው ያለፈው አባት ወደ ጃዊ የሚሄዱ ቄስ ነበሩ። የእነኝህ አባት ሙሉ አስከሬን እንደከዚህ ቀደሙ ወገኖቻችን ሞት ሁሉ ሙሉው አልተገኘም። አንዷ ሴት በፓዊ ሆስፒታል በመረዳት ላይ ትገኛለች። ኤዲዳ ማለት ግልገል በለስ ዙሪያ የምትገኝ በጣም ቅርብ ቀበሌ ናት። ከመተከል 132,000 ህዝብ ተፈናቅሏል። በመተከል በገጠር ቀበሌዎች የቀረ አማራ/አገው/ የለም! ሁሉም ተፈናቅሏል። በቻግኒ /ራንች/ብቻ ከ40,000 በላይ ተፈናቃይ አለ። ለእነዚህ ወገኖቻችን የዕለት ምግብ ለመደገፍ ደፋ ቀና በምንልበት ሰዓት ሞታችንም አልቆመም። ኮማንድ ፖስቱ ግን የት ነው? ምንጭ_ Minalbat Yitayew

Source: Link to the Post

Leave a Reply