You are currently viewing “ያላችሁበት ቦታ እንመጣለን፤ እናውቀዋለን፤ እናንተም ትታረዳላችሁ ይሉናል።” በምስራቅ ወለጋ ዞን ከቦነያ ቦሼ ወረዳ ላሎ ቀሬ ቀበሌ የተፈናቀሉ አማራዎች! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ያላችሁበት ቦታ እንመጣለን፤ እናውቀዋለን፤ እናንተም ትታረዳላችሁ ይሉናል።” በምስራቅ ወለጋ ዞን ከቦነያ ቦሼ ወረዳ ላሎ ቀሬ ቀበሌ የተፈናቀሉ አማራዎች! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ……

“ያላችሁበት ቦታ እንመጣለን፤ እናውቀዋለን፤ እናንተም ትታረዳላችሁ ይሉናል።” በምስራቅ ወለጋ ዞን ከቦነያ ቦሼ ወረዳ ላሎ ቀሬ ቀበሌ የተፈናቀሉ አማራዎች! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ከቦነያ ቦሼ ወረዳ ላሎ ቀሬ ቀበሌ ማንነት ተኮር ከሆነውና ከተደራጀው የጅምላ ግድያና እገታ አምልጠው የወጡ አማራዎችን በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በተባባሪዎቹ ታግተው ከቤታቸው ታግተው ስለተወሰዱት አሚማ ጠይቋቸዋል። ጥቅምት 25 ቀን 2014 ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ ነበር ከመኖሪያ ቤታቸው እያሉ በተደራጀውና በታጠቀው፣በመንግስት መዋቅር ባሉ አካላት ጭምር በሚደገፈው ኦነግ ሸኔና ተባባሪዎቹ ነው ታግተው ወደ ጫካ የተወሰዱት። ቀድሞ የተዘጋጀው በዝርፊያ ላይ የተሰማራ መንጋ ዘራፊ ቡድንም እስከሚበቃው ድረስ ንብረታቸውን ወስዷል። በጨካኞች ታግተው ከተወሰዱት እና ለእያንዳንዳቸው አንድ መቶ ሽህ ብር የተጠየቀባቸውም አማራዎች ስም ዝርዝር:_ 1) አቶ ሰይድ በያን፣ 2) አቶ ጌትነት ኢሳ፣ 3) አቶ መሀመድ ሀሰን፣ 4) አቶ መሀመድ አባቡ፣ 5) አቶ ሀሰን አባቡ፣ 6) አቶ ሰይድ ከበደ፣ 7) አቶ ኃይሉ መንገሻ፣ 😎 አቶ መልስ ከበደ፣ 9) አቶ ክንዱ ሀሰንና 10) ወ/ሮ እታለማው ይብሬ ናቸው። የሽብር ቡድኑ ሞጤ በተባለ አካባቢ በግልጽ የሚታወቅ ካምፕ አለው። የታጋች አማራዎችን ልጆች ይዘው እየተላቀሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ገንዘብ ከገደሉ በኋላም ይህን ያህል ገንዘብ ክፈሉ እንለቅላችኋለን የሚለው የተለመደ አውሬያዊ ተግባራቸው ከሆነ ሰነባብቷል። የታጋቾችን ስልክ በሙሉ ተቀብለው ቤተሰብ እና የላሎ ቀሬ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲደውሉ:_ “ያላችሁበት ቦታ እንመጣለን፤ እናውቀዋለን፤ እናንተም ትታረዳላችሁ” በማለት እያስፈራሯቸው መሆኑን ተናግረዋል። የቦነያ ቦሼ ወረዳ መስተዳድርም _”ከአቅሜ በላይ ነው እኔ ይህን ምንም ውሳኔ የምወስንበት አቅም የለኝም፤ ከአቅሜ በላይ ነው።ከፈለጋችሁበት ግቡ” እንዳላቸው ገልጸዋል። ከቦነያ ቦሼ ወረዳ ላሎ ቀሬ ቀበሌ ተፈናቅለው ወደ ጅማ ዞን ኖኖ በንጃ ከገቡት መካከል ከ60 በላይ የሚሆኑት ህዳር 3 ቀን 2014 አዲስ አበባ መግባታቸውን ለአሚማ አረጋግጠው ነበር። ይሁን እንጅ አየር ጤና ከመድረሳቸው ወደ ቀበሌ መስተዳድር መወሰዳቸውን ገልጸው አሚማ በስልክ ሲያነጋግራቸው ማን ነው የሚያነጋግራችሁ እያሉ ሲያሸማቅቋቸው እንደነበር ተረድቷል። በመጨረሻም የሚጠራ ስልካቸውን አያነሱም፤ ከሚዲያ ጋር የምትደዋወሉ ከሆነማ ውጡ በሚል እንዳስወጧቸውና በኋላ ላይ በቤተ ክርስቲያን መጠለላቸውን በአካባቢው የነበሩ ምንጮች አረጋግጠዋል። በተመሳሳይ በሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ወደ አዲስ አበባ አውቶብስ ተራ አካባቢ የገቡ እና እየገቡም በመሆኑ የሰብአዊ ጉዳይ ያገባናል የምትሉና መላው አማራዊ አደረጃጀቶች ሁሉ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በተጎጅዎች ተጠይቃችኋል። ከመካከላቸውም መንገድ ላይ የወለዱ እናቶች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply