ያልታበሰ እምባ! የታጋይ አስቴር ስዩም የፈተና ሕይወት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ…

ያልታበሰ እምባ! የታጋይ አስቴር ስዩም የፈተና ሕይወት! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ተወልዳ ያደገችው አስቴር/ቀለብ ስዩም የሕወሓት መራሹን ከፋፋይና ሴረኛ አካሄድን በቅጡ ተረድተው የድርሻቸውን ካበረከቱት የሴት ታጋዮች መካከል አንዷ ናት። ታጋይ አስቴር እብሪትና ድንቁርና ባሸነፈው እንዲሁም አማራ እና ኢትዮጵያ ጠል በሆነው የሕወሓት/ትህነግ ስርዓት እና መንግስት የጭካኔ በትር ካረፈባቸው ለአቋማቸውና ለአመኑበት ነገር ከማይምበረከኩት ፅኑ ታጋዮች መካከል አንዷ ስለመሆኗ ያሳለፈችውን የፈተና ህይወት ማየት በቂ ማስረጃ ነው። በ2007 ዓ.ም መጨረሻ ወራት ትግሉ እየተፏፏመ መምጣቱን ተከትሎ በአፋኙ ስርዓት የታሰረችው ፖለቲከኛ አስቴር ስዩም የ6 ወር ህጻን ልጇን ጥላ ቤቷ ማዕከላዊና ቃሊቲ ይሆን ዘንድ የግድ ሆነባት። ፖለቲከኛ አስቴር በርካታ የአማራ፣የኦሮሞና ሌሎች የኢትዮጵያ ልጆች በሚሰቃዩበትና የግፍ ግፍ በሚፈፀምበት ማዕከላዊ ተወስዳ ለወራት አያሌ በደሎችን አስተናግዳለች። የአዕምሮ ድህነት ጠፍሮ የያዛቸውና ስለነገ ማሰብ የተሳናቸው ባለጊዜዎች በድቅድቅ ሌሊት ሁሉ እየጠሩ ከመመርመር አልፈው ለመናገር የሚከብድ ግፍ እንደፈፀሙባት በአንደበቷ በተለያዩ ሚዲያዎች አጋልጣለች። አስቴር ለሀገርና ለወገን ስትል ዘር አጥፊውን ትሕነግ ፊት ለፊት አምርራ በመታገሏ ከእሷ አልፎ በቤተሰቦቿ ላይም ተደራራቢ በደል ተፈፅሞባቸዋል፤ በነሀሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በአዲስ አበባ የቂሊንጦ ቃጠሎ መከሰትን የሰማችው እናቷም “ልጄ ተቃጠለች” በሚል በድንጋጤ ምክንያት ባጋጠማት የጤና መታወክ ተጎድታ ማረፏ ይታወሳል። ሕዝባዊ ማዕበሉና ሁለገብ ትግሉ እየበረታ መምጣቱን ተከትሎ በ2010 ዓ.ም የተፈታች የነጻነት ታጋይ መሆኗም ይታወቃል። በአጭሩ አምባገነኑ የሕወሓት ስርዓት ወደ መቀሌ እንዲገፋ ብሎም ዛሬ ላይ ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ሁለገብ ታጋይዋ አስቴር ስዩም እና መሰሎቿ መልካም አስተዋፅኦ ነበራቸው ለማለት ይቻላል። ታጋይ አስቴር አሁንም የፈለገችው፣የታገለችለት ነጻነት፣እኩልነትና ፍትህ እውን ከመሆን ይልቅተረኝነት፣መንደርተኝነት፣አድርባይነት፣የሴራና የሸፍጥ አካሄድን እንደ መልካም ውርስ በመቀበል ሲነግስ ተመለከተች። በትሕነግ የደረሰባት በደልም ግንቦት 20 ተጠብቆ ዶክሜንታሪ ተሰርቶ ለሌላ ፖለቲካ ሲውል ተመለከተች፤ ይህንን አካሄድም በግልፅ ተቃወመች። አሁንም ትግል አይቆምም አለች። በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ በመሳተፍ ትግሏን ቀጥላለች። ታግሎ ያታግለኛል በሚልም ባልደራስ ፓርቲን በመቀላቀል በተለይም ዛሬ ላይ እንደእሷ በእስር ላይ ከሚገኙት ከባልደራስ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣አስካለ ደምሌና ከሌሎች ጠንካራ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ጋር በመሆን በተለይም በአዲስ አበባ የሚፈፀሙ ዘርፈ ብዙ በደሎችን በእልህ፣በቁጭትና በተቆርቋሪነት ስሜት ማጋለጡን ቀጠሉ። ምንም እንኳ በአቃቢ ህግ የተጠቀሰው ክስ ሌላ ቢሆንም ሲያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ በገዥው መንግስት ዘንድ እንዳልተወደደላቸው ብሎም በስተመጨረሻ በዋናነት ለእስር እንደዳረጋቸው ራሳቸው፣የፓርቲው አመራሮችና ሌሎች በርካታ ሰዎችም ሲናገሩ ይደመጣል። ያም ሆነ ይህ እነ አስቴር ስዩም ዛሬም ለዳግም እስር ተዳርገው ቤታቸው ቃሊቲ ከሆነ ወራቶች ተቆጥረዋል። በተለይም የአስቴር ስዩም እስር ታሪክ ራሱን ይደግም ዘንድ የግድ ይል ይመስል የ10 ወር ህጻን ልጇን ጥላ በቃሊቲ ማ/ቤት በእስር ላይ ትገኛለች። ለከፍተኛ የጀርባ ህመም መዳረጓና ተገቢ ህክምና አለማግኘቷም እየተነገረ ነው። ስለታጋይ አስቴር ስዩም “ያልታበሰ እምባ” ቤተሰቦቿንና የተለያዩ ወገኖችን በማነጋገር የተዘጋጀውን ዘጋቢ በአማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ/ በቅርብ ቀን ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply