ያማረ ቢሮ ብቻ ሳይሆን ያማረች አገር ለመገንባት እንሥራ – ጠ/ሚ ዐቢይ::

አዲስ አበባ፣መጋቢት 5፣2014 ያማረ ቢሮ ብቻ ሳይሆን ያማረች አገር ለመገንባት መሥራት አለብን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡ ዶክትር ዐቢይ ፓርቲው ዛሬ ባስመረቀው ዋና ጽህፈት ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ህንጻውን የሚመጥን ሥራ መስራት አለብን፤ ሀገር በዘይትና በስኳር የተነሳ ችግር ውስጥ እያለች ለመፍትሔው
መስራት ካልቻልን አስቸጋሪ ነው ብለዋል። በቢሯችን ልክ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የምንሠራ ሊሆን ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር በህንጻ ግንባታው ሦስት ሺህ ሠራተኞች ተሣትፈዋል ። ከነዚህ ውስጥ በሥራ ላይ እያሉ የሁለቱ ሕይወት ማለፉንም ጠቅሰዋል። ፓርቲው ያስመረቀው ህንጻ በአራት ሺህ 700 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል። ዛሬ የተመረቀው የብልጽግና ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት ግንባታው ሐምሌ ወር 2009 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በአጠቃላይ 895 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply