ያገለገሉ የእንጨት ስራ ውጤቶችን በአዲስ ለመቀየር የኢቢኤስ ፈርኒቸር ወደ እኔ ኑ ብሏል::ከታህሳስ 8 ጀምሮ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለ3 ወራት የሚቆይ ያገለገሉ የእንጨት ስራ…

ያገለገሉ የእንጨት ስራ ውጤቶችን በአዲስ ለመቀየር የኢቢኤስ ፈርኒቸር ወደ እኔ ኑ ብሏል::

ከታህሳስ 8 ጀምሮ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለ3 ወራት የሚቆይ ያገለገሉ የእንጨት ስራ ውጤቶችን በአዲስ የመቀየር ስራ ሊጀምር መሆኑን የኢቢኤስ ፈርኒቸር ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወንድማገኘው ደምሴ ተናግረዋል፡፡

የኢቢኤስ ፈርኒቸር የአስረኛ አመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድርጅቱ በ10 አመታት ውስጥ የደረሰበትን አሁናዊ ገጽታ፤ ለደንበኞች እና ለአጋሮቻቸው የማስተዋወቅ እና ምስረታወን አስመልክቶ በዓሉን በጋራ ለማክበር ያለመ ዝግጅት አከናውኗል፡፡

አቶ ወንድማገኘው እንደገለጹት፤ያገለገሉ የእንጨት ስራ ውጤቶች ለገበያ ሲቀርብ በዝቅተኛ ዋጋ የሚሸጥ መሆኑ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪና እንግልቱ ዜጎች የቤት ንብረታቸውን እንዳይቀይሩ ምክንያት እንደሚሆንባቸው ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም የሌሎች ሀገራት ተሞክሮን በመውሰድ ያገለገሉ ምርቶችን ወደ ፈርኒቸሩ በመውሰድ በባለሞያ ምርቱ ከተተመነ በኋላ አዲስ የእንጨት ስራ ውጤቶች የሚወስዱበት ሁኔታ መፈጠሩን ተገጿል፡፡

በምስረታ በዓሉም ላይ የማህበረሰብ አንቂ ስራዎች ላይ የሚሳተፍ ቲክቶከር ብሩክሲቲ የኢቢኤ ፈርኒቸር የክብር አንባሳደር ሆኖ ተመርጧል፡፡

በሀገር ውስጥ የሚገኙ ለእንጨት ስራ የሚያገለግሉ ግብአቶች እጥረት እንደተግዳሮት የተጠቀሰ ሲሆን፤ በፈርኒቸሩም 200 የሚሆኑ ሰራኞች የስራ እድል ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡
ኢቢኤስ ፈርኒቸር የህክምና ተቋማትን፣ትምህርት ቤቶችን እና የመንግስት ተቋማትን በእንጨት ስራ ውጤቶች እንደገና የማደራጀት ስራዎችን በመስራት የማህበራዊ ተሳትፎውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ታህሳስ 02 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ
መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8)

Source: Link to the Post

Leave a Reply