
ይህ ድርጊት ከሌሊቱ 6:30 ነው! የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ “ከባለቤቴና ከልጆቼ ጋር አገር ሰላም ብዬ ተኝቻለሁ። የትልቅ ተሽከርካሪ ድምፅ ወደ ቤታችን አቅጣጫ ሲመጣ ይሰማኛል። መንገድ ስቶ የመጣ የጭነት ተሽከርካሪ መስሎኝ ደንግጨ ከአልጋዬ ብድግ ስል ቤታችንን ከወደ በሩ በኩል አንድ ግሬደር መብራት አጥፍቶ እያፈረሰው ነበር። ልጆቼም ባለቤቴም እኔም ራቁታችንን ተነሳን ። መውጫ መንገድ አጣን። የቤቱ ፍርስራሽ አቧራ አፍኖናል ። ከውጭ ጩኸታችንን የሰማ ሰው የግሬደሩን ኦፕሬተር ተማፅኖ አስቆመው። አሁን ከፍርስራሹ ውስጥ ራቁታችንን ወጥተን ቤታቸው ወዳልፈረሰባቸው ሰዎች ቤት ቢያስጠጉን እየሄድን ነው” በዚህ ደረቅ ሌሊት በአዲስ አበባ አቅራቢያ ጣፎ አካባቢ ቤታቸው በላያቸው ላይ እየፈረሰባቸው የሚገኙ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ የገለፁት ነው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post