ይድረስ፡ለመምህር፡ጳውሎስ፡ሚልኪያስ፣ ጉዳዩ፡ስለ፡”የኦሮሞና፡የአማራ፡ሕዝብ፡እውነተኛ፡የዘር፡ምንጭ”

ጉዳዩ፡ስለ፡”የኦሮሞና፡የአማራ፡ሕዝብ፡እውነተኛ፡የዘር፡ምንጭ”፤ስለ፡አድረግኸው፡አቃቂር።

በመጀመሪያ፡የከበረ፡ሰላምታችን፡ይድረስህ።በመቀጠልም፣አንተም፡እንደ፡ገለጽከው፡”እንደ፡ጣፋጭ፡ዳቦ”፡በኢትዮጵያውያን፡ተወድዶ፡በመሸጥ፡ላይ፡ላለው፡መጽሐፍ፡አቃቂርህ፡እጅግ፡በጣም፡የከረረ፡ጥላቻ፡አጅቦ፡በመቅረቡ፣ወጣቱን፡ደራሲ፡አሳስቦት፡የጻፈልህንም፡መልስ፡በጥሞና፡አንብበናል።በድጋሚ፡መልስ፡ሊሰጥህ፡ግዜ፡እንደ፡ሌለውም፡ገልጾ፡ጽፎልልህ፡ልትቀበለው፡አልቻልክም።ለዋቢ፡ያቀረባቸውንም፡መረጃዎች፡ውድቅ፡አድርገህበታል።የባሕታዊ፡መሪራስ፡አማን፡በላይን፡መጻሕፍት፡ወስደው፡የራሳቸው፡ግኝት፡አስመስለው፡የጻፉም፡ነበሩና፡አሁን፡ፍቅሬ፡ቶሎሳ፡ጂግሳ፡ከመሪራስ፡ምንጮች፡ማግኜቱን፡ሳይደብብቅ፡በመጻ ፉ፤ከነ፡አካቴውም፡የመሪራስንም፡ግኝት፡”አባይ”፡በማለት፡ፈርጀኸዋል።

በርግጥ፡የፍቅሬ፡አቀራረብ፡ከአዛኞቻችሁ፡ባለ፡ታሪከኞች፡ለየት፡ባላ፡መልኩ፡ቦታውን፡እረግጦ፡በማጣራት፡ጭምምር፡ተመራምሮ፡ለማቅረብ፡ሞክሯል።በውጭ፡አገር፡ደራሲዎች፡የቀረቡ፡ኢትዮጵያ፡ነክ፡ስሕተቶች፡መትታረም፡እንዳለባቸውም፡ያምናል።ሆኖም፡ምሁር፡ፍጹም፡ሰው፡አይደለህም፡ሲባል፡በማያምንበት፡ግድዴታ፡ይኸን፡ካላቀረብክ፡”እርሱንም፡መጸሐፉንም፡ቆሻ ሻ፡ማጥጠራቀሚያ፡ቅርጫት፡ውስጥ፡ክተቱት”፡መብባሉ፡ተገቢ፡ነወይ?።ልትወልደው፡የምትችለው፡ወጣት፡ተመራማሪ፡ሊተካህ፡ሲመጣ፡እና፡ስሕተት፡ካደረገ፡ልታርርመውስ፡አይገባም፡ነበረ፡ወይ?።እርሱ፡ታሪክን፡ተመራምሮ፡በወገን፡ደራሲዎቹ፡የሚኮራ፣አንተ፡የውጭ፡አገር፡ደራሲዎችን፡አምላኪና፡አሰር፡ገሠሥ፡ሳትለይ፡መዝጋቢ፡መስለህ፡እየታየኸን፡ነው።አንድ፡ጣትህን፡ወደ፡ሰው፡ስትቀሥሥር፣ሦስቱ፡ወደ፡አንተ፡መቅቀሰራቸውን፡አትዘንጋ።

መምህር፡ጳውሎስ፡ሆይ!፡አስተማሪና፡ደራሲዎች፡ፍጹም፡ሰው፡አይደላችሁምና፡የአንተን፡ጉድፍ፡ፈልልጐ፡መጻፍ፡ከተፈለገ፡ብዙ፡ዓይነት፡ችግር፡እንዳለብህ፡ስለሚታወቅ፡በሰው፡ላይ፡እንደዚህ፡ዓይነቱን፡ሕዝብ፡ወድዶ፡ሊያነብበው፡አቅራቢውን፡ደራሲ፡ማስቸገሩን፡ብትተወውና፡አንባብያን፡የራሳቸውን፡ውሳኔ፡ቢወስዱ፡መልካም፡ይመስለናል።ወቅቱ፡ሕዝብን፡አስተባብሮ፡የአምባገነኖችን፡ዘረኛ፡አሰተዳደር፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡አስወግዶ፡የሕዝባዊ፡ፍትሕ፡ሥነ፡መንግሥት፡የሚመሠረትበትን፡ሁኔታ፡መፍጠ ር፡እንጂ፡የሚከፋፍልና፡አጨቃጫቂ፡ሐሣብ፡የሚመረጥበት፡አይደለም።

አቃቂርህን፡ያነበብነው፡መጽሐፉን፡ከማንበባችን፡በፊት፡ነብበረ።እኛ፡ሁኔታህን፡አንብበን፡ስናስበው፡ግን፡ግራ፡ያጋብባል።የደራሲውን፡መብትም፡ተጋፍተህ፡በአንተ፡ስልት፡ካልሆነ፡የሌላውን፡ላለመቀበል፡ያቅቀድክ፡ትመስላለህ።እናም፣መጽሐፉ፡ከዚህ፡ቀድደም፡በኢትዮጵያውያንና፡ኢትዮጵያ፡ላይ፡ሲለፈፍ፡የነበረውን፡ነውር፣ክብር፡ባልለው፡አቀራረብ፡እያስተማረን፡ይመስለናል።ያ፡ለምን፡እንደተሰወረብህ፡ግልጽ፡አልሆነልንም።

ጽሑፍህን፡ካነበብን፡በኋላ፡ይህን፡መልእክት፡ልንጽፍልልህ፡የወደድንበት፡ምክንያት፣መጽሐፉ፡ሕዝብን፡እያፍፋቀረ፡ባልለበትና፡ኢትዮጵያውያንን፡ያቀራርባል፡ተብሎ፡በታሰበበት፡ወቅት፡የአንተ፡መቃወም፡ኢትዮጵያ፡ውስጥ፡ላለው፡አገዛዝ፡ደግጋፊ፡እንደሆክ፡አመላካች፡ነው፡ብለን፡ስለምንጠረጥር፡ሕዝብ፡በምን፡እንደሚገምምትህ፡ለመጠቆምም፡ነው።ከአገርህ፡እርቀህ፡ብዙ፡ዓመታትን፡በማሳለፍህ፡ይሆናል፡ብሎ፡ለጠቀሰልልህ፡መልስ፡ስትሰጥ፤”ተከፍሎኝ፡ሄጀ፡አዲስ፡አበባ፡መካነ፡አእምሮ፡አስተምሪያለ ሁ”፡ያልከው፡አስገራሚ፡ነው።ዐርባ፡ሁለት፡ቋሚ፡መምህራን፡ከተባረሩበት፡ተቋም፡ያውም፡ተከፍሎህ፡ማስተማርህ፡ለአገሪቱ፡አስተዳደር፡ምን፡ያህል፡ቅርበት፡እንዳልለህ፡ያሳያል።

ስለዚህ፣አንተን፡በድረገጽ፡ማስሳጣቱ፡ተገቢ፡መስሎ፡ስላልታየን፣እንደዚህ፡በግልል፡አድራሻህ፡ጽፈን፡ፍቅሬንና፡የኢትዮ ጵያን፡ሕዝብ፡ይቅርታ፡ጠይቀህ፡ኢትዮጵያዊ፡ኅብረት፡የሚፈጠርበትን፡መንገድ፡እንድታስብ፡ብታደርግ፡ጠቀሜታ፡አልለው፡እንላለንና፡ታረቁ።

 

ኢትዮጵያ፡ከነ፡ክብረ፡ነፃነቷ፡ለዘላለም፡ትኑር።አሜን።

 

ኢትዮጵያዊው፡ዜናማርቆስ፡መርሐ፣

ካናዳ።

 

ግልባጭ፦ ለገጣሚና፡ታሪክ፡ተመራማሪው፡ፍቅሬ፡ቶሎሳ፡ጂግሳ፣

የተባበሩት፡አመሪካ።

የካቲት፡፩፡ቀን፡፪ሺ፱፡ዓመተ፡ምሕረት።

Leave a Reply