ይድረስ ለሃያላኑ የፋኖ መሪዎች ————– ከሸንቁጥ አየለ ======== ለአርበኛ አሰግድ … ለአርበኛ መከታዉ ለአርበኛ ሻለቃ መሳፍንት ለአርበኛ ዘመነ ለአርበኛ ምሬ እንዲ…

ይድረስ ለሃያላኑ የፋኖ መሪዎች ————– ከሸንቁጥ አየለ ======== ለአርበኛ አሰግድ … ለአርበኛ መከታዉ ለአርበኛ ሻለቃ መሳፍንት ለአርበኛ ዘመነ ለአርበኛ ምሬ እንዲሁም ለመላዉ የፋኖ ሀይላት ==================== ባላችሁበት እንዴት ናችሁ ? መድሃኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሀይሉን ከእናንተ ጋር ያድርግ።ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን ዘሩን ከምደር ሊያጠፉት አዋጅ ያወጁበትን የአማራ ህዝብ ታድኑት ዘንድ እንዲሁም ትፈርስ ዘንድ ዉል የተያዘባትን ቅድስት ኢትዮጵያን ከመፍረስ ትታደጓት ዘንድ እግዚአብሄር ጥበብና ሀይል ይስጣችሁ። ======== ========= በፋኖዉ እንቅስቃሴ ዉስጥ እንደ አሰግድ አይነት የምናብ ሀይል ያላቸዉ ጀግኖች፥ እንደ መከታዉ አይነት ወፍ አርግፍ ጦረኞች ፡ እንደ ሻለቃ መሳፍንት አይነት ጽኑአን አርበኞች ፥ እንደ ምሬ አይነት ትሁት ተዋጊዎች ፥ እንደ ዘመነ ካሴ አይነት በእዉቀት እና ህዝብን ተናግሮ በማሳመን ክህሎት የታነጹ አርበኞችን ሳይ ልቤ በሃሰት ይዘላል። ልክ እንደ እኔ ሁሉ ሚሊዮኖች ይሄን የፋኖ ንቅናቄ በታላቅ ተስፋ ይጠብቁታል። ======================== ደራሴ አሰግድ መኮንን 27 አመታት ወያኔን በብእሩ ተዋግቶታል። በዚህ አምስት አመታት ደግሞ ትግሉን ወደ አርበኝነት ደረጃ ከፍ አድርጎ ስለ ህዝቡ ነፍጥ አንግቦ ፋኖ ሆኗል። ይሄም የሚያስከብረዉ እና የሚያስወድደዉ ታላቅ ህዝባዊ አደራን ለመቀበልም ቆራጥ መሆኑን የሚያስመሰክር ነዉ። ይሄን መሰል ረዥም ተጋድሎ ለማድረግ ብዙዎች አልታደሉትም ወይም ሊሸከሙት አልቻሉም።ወይም ብዙዎች ደክሟቸዋል። ብዙዎቹ የደራሲ አሰግድ መጽሃፍት የአርበኝነት ብቻ ሳይሆኑ ሀገር የማዳን ትንቢታዊ ጭብጥን የያዙ ጭምር ናቸዉ።በተለይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1996 ዓም ያነበብኩት መጽሃፉን ሁሌም አስታዉሰዋለሁ። በዚህ ልብ ወለድ መጽሃፉ ዉስጥ ኢትዮጵያን ለማዳን ስለሚነሳዉ ንጉስ በማካተት ሌሎች አስደማሚ ገጸባህሪያትን ይተርክልናል። ይሄም የመጽሃፉ ታሪክ አሰግድን ባሰብኩ ቁጥር ትዝ ይለኛል።የታሪኩ ጭብጥና ምናባዊ ጉልበቱም ያስገርመኛል። ከብዙ አመታት ብኋላ የተረዳሁት ነገር አሰግድ ጀግና ጸሃፊና ጀግና ተራኪ ብቻ ሳይሆን እራሱም ጀግና መሆኑን ነዉ። በፋኖዉ እንቅስቃሴ ዉስጥ እንደ አሰግድ አይነት የምናብ ሀይል ያላቸዉ ጀግኖች፥ እንደ መከታዉ አይነት ወፍ አርግፍ ጦረኞች ፡ እንደ ሻለቃ መሳፍንት አይነት ጽኑአን አርበኞች ፥ እንደ ምሬ አይነት ትሁት ተዋጊዎች ፥ እንደ ዘመነ ካሴ አይነት በእዉቀት እና ህዝብን ተናግሮ በማሳመን ክህሎት የታነጹ አርበኞችን ሳይ ልቤ በሃሰት ይዘላል። የዘር ፍጅት የታወጀበት የአማራ ህዝብ እንድትፈርስ የተበዬነባት ቅድስት ኢትዮጵያ ዳግም ነጻ ሀገር ሆና እንደምትመሰረት ተስፋ አደርጋለሁ። ፋኖ መከታዉ የኦነግ/ኦህዴድ ጦር የሸዋ ከተሞችን በስፋት ባወደመበት ወቅት ዘራፍ ብሎ በመነሳት ኦነግ/ ኦህዴድን ቀጥቅጦ በመምታት በታልቅ ጀብዱ የአማራን ህዝብ አንገት ቀና ያደረገ እንቁ አርበኛ ነዉ። የሻለቃ መሳፍንት መላዉ የአማራ ፋኖ ይወለድ ዘንድ ወያኔን ገትሮ በመዋጋት ብቻ ሳይሆን የአማራ ወጣቶችና አርበኞች የሞራል ካስማ የጉዞ ቀንዲል የሆነ እስደማሚ ሀያል አርበኛ ነዉ። በሰላማዊ ትግል ከመኢአድ እስከ አማራ ተጋድሎ ብሎም እስከ ፋኖ እንቅስቃሴ የዘለቀ ለህዝቡ የታመነ ጽኑ መሪ ነዉ። ምሬ ወዳጆ በጥበብ የታሸ እስላም ክርስቲያኑን ሀያላን የአማራ ጀግኖችን በማስተባበር ኦነግ/ኦህዴድን በጢር ብቻ ሳይሆን በስነልቦና ድቀት ዉስጥ የከተተ ገራሚ ቶረኛ ነዉ።በዚህም ኦነግ/ ኦህዴድ በወሎ በሙስሊምና ክርስቲያን መሃከል ጸብ ዘራሁ ሲል ምሬ ጠቢቡ ከአርበኞቹ እነ ሙሃባ ጋር በመሆን የኦነግ/ኦህዴድን ተንኮል አኮላሽተዉበታል። እንግዲህ ማን ቀረ? አርበኛ ዘመነ ካሴ አደለምን? ስለሱ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ ጽፌ አለሁ።በስሱ ግን ላንሳዉ።ዘመነ ካደረገዉ ሃያል እና ታሪክ ሁል ጊዜም ከፍ አድርጎ ከሚዘግብለት ስራዉ ዉስጥ ” የአማራ ወጣት ካሁን ብኋላ ታጠቅ፥ ፋኖ ሁን።አለዚያ የአማራ ዘር ቆመህ ማለቁ ነዉ” ብሎ በሚያስገመግም ድምጹ እንደ ጥልቅ ዉቃያኖስ በረጋዉ የገለጻ ስልቱ በመላዉ የአማራ ወጣት ዉስጥ የለቀቀዉ ሞገዳዊ የጀግና አስተምህሮቱ ነዉ።ያስተማረዉንም ትምህርት ድርጅት መስርቶ እየተፋለመ ይሄዉ በተግባር በመኖር ለወጣቱ እያሳዬ ነዉ።ይሄም ድንቅ ነዉ ! እናም በፋኖዉ እንቅስቃሴ ዉስጥ እንደ አሰግድ አይነት የምናብ ሀይል ያላቸዉ ጀግኖች፥ እንደ መከታዉ አይነት ወፍ አርግፍ ጦረኞች ፡ እንደ ሻለቃ መሳፍንት አይነት ጽኑአን አርበኞች ፥ እንደ ምሬ አይነት ትሁት ተዋጊዎች ፥ እንደ ዘመነ ካሴ አይነት በእዉቀት እና ህዝብን ተናግሮ በማሳመን ክህሎት የታነጹ አርበኞችን ሳይ እርግጠኛ የሆነ አንድ ነገር ይታዬኛል። ይሄዉም ፋኖዉ የኢትዮጵያ የነጻነት ሰራዊትን በፍጥነት በመመስረት ብሎም ልዩ ልዩ ነገዶችን በማሳተፍ ነጻይቱ ኢትዮጵያ የምትመሰረትበትን አስተማማኝ መሰረት መጣል ይችላል። እስካሁን አብዛኛዉ የአማራ ክልል በሀያላኑ ጦረኞች በፋኖዎች ቁጥጥር ስር ገብቷል።። ይሄም ማለት በአስተማማኝ የኢትዮጵያ ነጻነት ሀይላት ሰራዊት ቢመሰረትና አንድ እርምጃ ወደ አዲስ አበባና ልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አድማሱን ቢያሰፋ መላ ሀገሪቱን በቁጥጥር ስር ማዋል ይችላል። የኦነግ/ኦህዴድ ጦር እንደሆነ ህጻንና ሴት ከማረድ ዉጭ ቆሞ እንደማይዋጋ ይታወቃል። እናም ሸዋ ላይ አትግባብኝ ፥ ጎጃም ላይ አትግባብኝ፡ ጎንደር ላይ አትግባብኝ ወሎ ላይ አትግባብኝ ከሚል ራእይ ገዳይ ህሳቤ በመዉጣት ወደ ትልቁ ወድ ኢትዮጵያ ማማ ላይ ራእይን መትከል ይገባል።ታላቁ ራእይም ታላቁን ሀገራዊ ድል ይወልዳል። ጥበብ እዚህ አለ። የጨረስከዉን ትግል ወደኋላ መመለስ ከፈለግህ ሸዋ የኔ ፥ ጎጃም የኔ ፥ ወሎ የኔ፡ ጎንደር የኔ እያልክ እያንዳንድህ ክፍለሃገርህን አንቀህ በክፍለሃገርህ ዉስጥ ደግሞ ዞር ብለህ እርስ በእርስህ ተናንቀህ ባለህበት ርግርጥ። ጥበብን ስማ። ጥበብን ስማ ! ጥበብን ስማ ! ማን ይነግሳል የሚለዉን እርሳዉ። የሚመራህን እግዚአብሄር ያዉቅልሃል።ወይም አንደምታ ጸሃፊያን አባቶችህ እንደሚሉት አንድም ሁልህም ተሰብስበህ የኢትዮጵያ ነጻነት ሰራዊትን ከመሰረትክ ብኋላ በሰለጠነዉ አለም በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስልት እርስ በርስ እየተወያየህም እየተመካከርክም ትመራረጣለህ።አንድም ጊዜዉ ሲደርስ ጊዜዉ የሚያሳዉቅህ ብዙ ጥበብ ይኖራልና ይሄ አያስጨንቅህ።ይልቅስ ህዝብህ መከራ ዉስጥ ገብቷል እና ወደ ታላቁ ማማ ላይ የሚያወጣህ ራ eይህን ትከለዉ። ከዚህ ዉጭ ወንድምህ ቢመክርህ ወይም የቡድንህ ሰዉ ቢነግርህ ወይም የሰፈርህ ወይም የክፍለ ሃገርህ ሰዉ ቢመክርህ አትስማ። ጥበብን ስማ። ጥበብን ስማ ! ጥበብን ስማ ! የፋኖ ሀይል ሁሉ በፍጥነት በጋራ መክረህ እራስህን ወደ ኢትዮጵያ ነጻነት ሰራዊ ከፍ በማድረግ የራእይ ከፍታህን ወደ ታላቁ ማማ ላይ ስቀለዉ። ==== ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች !

Source: Link to the Post

Leave a Reply